በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞረትና ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ የደረሰው ጥቃት


ሞረትና ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ
ሞረትና ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ ከ20 ዓመት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ በቆየ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን አጥቢያ ላይ የደቦ ጥቃት መድረሱን እና ሦስት ምዕመናን መጎዳታቸውን የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቤ ይልማ ዋቄ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። በጥቃቱም ቤተእምነቱ ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን ገልፀዋል።

በተጨማሪም በዚሁ ከተማና በአካባቢው ለሚገኘው ማኅበረሰብ የነፃ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ወደ ስፍራው ተጉዘው የነበሩ የአገር ውስጥና የውጭ አገር የሕክምና ቡድኖች በሕክምና ዕቃቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው የወረዳው አስተዳዳሪ ተናግረዋል። አያይዘውም በንብረት ላይ እንጂ በሰው ላይ አንድም የደረሰ አደጋ የለም ብለዋል። (ዝርዝሩን ያዳምጡ)

በሞረትና ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ የደረሰው ጥቃት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:17 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG