በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቅድመ ምርጫ አቤቱታዎችና - የኢትዮጵያ መንግሥት ቅድመ ዝግጅት


የቅድመ ምርጫ አቤቱታዎችና - የኢትዮጵያ መንግሥት ቅድመ ዝግጅት
የቅድመ ምርጫ አቤቱታዎችና - የኢትዮጵያ መንግሥት ቅድመ ዝግጅት

ስድስተኛው የ2012 ዓ.ም ሃገር አቀፍ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሆን ቀጠሮ ተቆርጧል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ፣ ተአማኒና ውጤቱም ተቀባይነት የሚኖረው እንዲሆን ለማድረግ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር ተባብሮ ለመሥራት እየተጋ መሆኑን ይናገራል። በሌላ በኩል ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤታቸው ከወዲሁ እያቀረቡ ነው።

የቅድመ ምርጫ አቤቱታዎችና - የኢትዮጵያ መንግሥት ቅድመ ዝግጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:34:46 0:00


የፓርቲዎቹ ተወካዮች ለቅድመ ዝግጅት ወደ ተለያዩ ከተሞች ሲሄዱ በሌላ ፓርቲ ደጋፊዎችና በመንግሥት የፀጥታ አካላት ትንኮሳ እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለፅ እየከሰሱ ናቸው።

እየተወቀ ያለው ደግሞ አንድም በመንግሥትነቱ አንድም ደግሞ በተፎካካሪ ፓርቲነቱ ተፅኖ እያሳደረ ነው የሚባለው ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ነው።

ፓርቲው ግን እንደ መንግሥትም እንደ ፓርቲም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ፣ ተአማኒና ውጤቱም ተቀባይነት የሚኖረው እንዲሆን ለማድረግ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር ተባብሮ ለመሥራት እየተጋ መሆኑን ይናገራል።

ከምርጫው መምጣት ጋር እየተሰሙ ያሉ አቤቱታዎችና የኢትዮጵያ መንግሥት ዝግጅትን ጽዮን ግርማ በተከታዩ ዘገባ ትዳስሰዋለች። ኦፌኮ ፣ ኦነግ፣ ኢዜማ፣ አብን፣ ሕወሓት እና ብልፅግና በዘገባው ውስጥ ተካተዋል።(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG