በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተለይ በምሥራቅ ደንቢያ እና ጭልጋ አካባቢ ግጭት መቀጠሉ ተገለፀ።
የህግ አማካሪም ሆነ ጠበቃ ማግኘት እንዳልቻሉ የተናገሩት ባሕር ዳር ላይ በሕግ ሥር የሚገኙት የቀድሞ ባለሥጣን አቶ በረከት ስምዖን መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠይቀዋል።
በአማራ ክልል የዳኞች ማኅበር ተቋቋመ
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር መስራች ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ስርዓተ ቀብር፣ ዛሬ በትውልድ ቦታቸው መርሃዊ ከተማ ተፈፀመ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጠቅላላ ጉባዔ፣ የግንባሩን ሊቀ መንበርና 7 የሥራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ አጠናቀቀ።
የፌደፌሽን ም/ቤት በክልሎች መካከል የሚፈጠረውን የወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ሲገባው በአማራ ክልል በህጋዊ መንገድ የቀረበ የማንነት ጥያቄ የለም ብሎ መደምደሙ በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል አላስፈላጊ ውዝግብ እንዲፈጠር እያደረገ ነው ሲሉ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የፕሬዚዳንቱ የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪ አቶ መርሃፅድቅ መኮነን ተናገሩ።
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በህግ ጥላ ሥር የሚገኙት የእነ አቶ በረከት ለፍርድ መቅረብ ከለውጡ ጋር በተያያዘ በህዝብ ዘንድ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቶ የነበረውን የህግ የበላይነት መሥመር እየያዘ መሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ አንዳንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
ሁለቱ የቀድሞ የብአዴንና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በጥረት ኮርፕሬት ፈፅመዋል ተብለው በተጠረጠሩበት የኃብት ብክነት ወንጀል ነው።
በክልልም ሆነ በሀገርቀፍ ደረጃ በዳኝነት የሙያ ዘርፍ የመጀመሪያ ማኅበር ነው ተብሏል፡፡
ስፖርት የሰላም፣ የአብሮነት የወዳጅነት ማሳያ ነው የፖለቲካ ማራመጃ አይደለም ሲሉ የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገለፁ፡፡
“ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት 'ከልመናና ከጎዳና ህይወት እናወጣችኃለን' በሚል ሰበብ ከጎዳና ላይ ታፍሰንና ተጋፈን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ብንወሰድም፤
“ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት 'ከልመናና ከጎዳና ህይወት እናወጣችኃለን' በሚል ሰበብ ከጎዳና ላይ ታፍሰንና ተጋፈን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ብንወሰድም፤ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለሰባዊ መብት ጥሰት ተዳርገን ቆይተናል” ሲሉ ከአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ አዲስ ራይ ማሰልጠኛ ተቋም ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ የመጡ ወጣቶች ገለፁ።
"ከሆስፒታሉ ካርድ ከማውጣት ውጭ ምንም ዓይነት አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም። ምርመራ ከግል ሆስፒታል አድርጉ፣ መድሃኒት ከውጭ ግዙ ነው የምንባለው" ሲሉ በባህር ዳር ከተማ የፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተገልጋዮች ገለፁ።
ከዘጠኝ ክልሎች የተወጣጡ ሃያ ሁለት እናቶች - በባህር ዳር
በዕርዳታ በተገኘ ገንዘብ ባጃጅ ገዝቶ በመስጠት ሥራ ያልነበራቸው ያላቸውን ሃያ አምስት ወጣቶች ሥራ ማስጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ የጥቃቅንና የአነስተኛ ንግዶች ልማት መምሪያ ገልጿል።
የአማራና የቅማንት ሕዝብ በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማናትና በሥነ ልቦና አንድ ሕዝብ ነን፣ ሊለያዩን የሚሹ ወገኖችን ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ስለ ሰላም እንሰራለን ሲሉ በጎንደር በተደረገው የሰላም ውይይት ላይ የተገኙ የሁለቱም ወገን ተሳታፊዎች ተናገሩ።
ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ካማሽ ዞን፣ ያሶ ወረዳ ከሚገኘው ቀያቸው ተፈናቅለው ባህርዳር ከተማ የገቡ አምስት መቶ ተፈናቃዮች ከክልሉ መንግሥት ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገልፀው ቅሬታ አቀረቡ።
የአማራ ሕዝብ በአለፉት ጊዜያት በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኮስሶ እንዲታይ በውሽት ትርክት ክብሩ ዝቅ እንዲል ሲደረግ፣ መኖሩ ቁጭትን ፈጥሮብናል ይላሉ የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በደንቢያና ጭልጋ በቅማንትና አማራ ብሄር ተወላጆች መካከል ከአራት ቀናት በፊት በተቀሰቀሰ ግጭት ከሥድስት በላይ ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፀ።
ተጨማሪ ይጫኑ