ህዝቡ ራሱ ታግሎ ያመጣውን ሰላምና ነፃነት ወደ ኃላ እንዳይቀለበስ ከመንግሥት ጎን ሊቆም ይገባል ሲል የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ገለፀ።
ጎንደር ዩንቨርስቲ በችግር ምክንያት የከፍተኛ ትምህርታቸውን መቀጠል ላልቻሉ ለ60 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እየሰጠ መሆኑን የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፀ። ከ60ዎቹ ውስጥ 40ዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡
ጤና ነክ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሉባልታዎች በተለይ የክትባትና የምርምር ሥራዎችን ለመሥራት እንቅፋት ሆኖብኛል ይላል የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ።
በጣና ቂርቆስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳት በእንቦጭ አረም ምክንያት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ ተናገሩ።
ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ሰላምን ለመስበክ በራሳቸው ፈቃድ የተሰባሰቡ የሰላም እናቶች ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በመገኘት ለአዲስ አበባና ለባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ስለ ሰላም ሰብከዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ የአሥር ሚሊዮን ብር ልገሳ በከተማው አስተዳደር ስም አበረከቱ፡፡
የትምህርት ተቋማት የእውቀት እንጅ የግጭት ማዕከል እንዳልሆነ ተማሪዎች ተረድተው የመጡበትን ዓላማ ለማሳካት ቅድሚያ መስጠት አለባቸው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለፁ።
"ወሰንና የማንነት ጥያቄን በህገ መንግሥቱ አስመልሳለሁ" ይላል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ በቅርቡ አካሂዶት በነበረው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር ትላንት ከባህርዳር ከንቲባ ጋር በተለያዮ ጉዳዮች ላይ እንደመከሩ ተገለፀ።
የወልቃይት ህዝብ ማንነት እኛ የወልቃይት ተወላጆች እንጂ ሌላ አካል እንዲገልፅልን አንፈልግም ሲሉ ቪኦኤ ያነጋገራቸው የወረዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የፌዴሬሽን ም/ቤት በማንነት ዙርያ እያወጣው ያለው መግለጫ እንደ ተቋም ገለልተኛ ያልሆነና ወገንተኝነት የሚታይበት ነው ሲሉ የወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሎኔል ደመቀን ጨምሮ አንዳንድ የወልቃይት ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) አንድ ፓርቲ ሆነው በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማልያ መሪዎች ስለአካባቢያቸው ሰላምና ምጣኔ ኃብት መምከር በአፍሪካ ቀንድ ለሚታየው የስደትና የድኅነት ማዕበል መረጋጋት ይፈጥራል ሲሉ አንዳንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ጠ/ር አብይ አሕመድ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እናየሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ አመሻሹን ባህርዳር ከተማ ገብተዋል፡፡ መሪዎቹ ባህርዳር ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አደርገውላቸዋል።
ጠ/ር አብይ አሕመድ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ አመሻሹን ባህርዳር ከተማ ገብተዋል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ዛሬ ጎንደር ከተማ ገቡ፤ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቀባበል አደርገውላቸዋል ሲሉ መንግታዊ ዜና አውታሮች ዘገቡ።
በምዕራብ ጎንደር ዞን በተለይ መተማ አካባቢ ሰሞኑን ሁከት ተፈጥሮ ነበር። በሁከቱ የሰው ህይወት ጠፍቷል ንብረትም ወድሟል።
የእንቦጭ አረም በእለት ከእለት ኑሮአችን ላይ የከፋ ችግር እየፈጠረብን ነው ሲሉ የአካባቢው አርሶ አደሮች ገለፁ።
ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው ጎንደር ከተማ በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙት ተፈናቃዮች መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ ይስጠንና ወደቀያችን እንመለስ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ