በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ውግዘት


የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ውግዘት
የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ውግዘት

የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሰሞኑን በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በአምልኮ ተቋማት ላይ የደረሰውን ቃጠሎና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰውን የህይወትና የአካል ጉዳት አውግዟል።

ጉባዔው የተሰበሰበው ባሕር ዳር ላይ ሲሆን መሪዎቹ ትናንት መግለጫ ሰጥተዋል። "የሰው ልጅ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ውድ ፍጡር ነው፡፡ ምድርም የተሰራችው የሰው ልጅ እየተተካካ እንዲኖርባት እንጂ በዘር ተቧድኖ እንዲከፋፈላት አይደልም፡፡ ህዝብም ህዝብን ጠባቂ እንጂ ህዝብን ገዳይ አይደለም፡፡” ይህንን ያሉት የአማራ ክልል ሐይማኖቶች ጉባዔ የቦርድ ሰብሳቢ መልአከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም ናቸው፡፡

“የሐይማኖታችን አስተምሮ እንደሚለው ዘረኝነት ጥንብ ናታት ራቃት” - ያሉት ደግሞ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ሼህ ሰኢድ መሀመድ ናቸው፡፡ የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ሰሞኑን በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በቤተ እምነቶች ላይ የደረሰውን ቃጠሎና በንፁሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን የህይወትና የአካል ጉዳት የሐይማኖት ጉባዔው አውግዟል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ውግዘት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG