በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ግጭት የተፈናቀሉ በከፋ ችግር ውስጥ ናቸው


በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች በቅርቡ በተፈጠረው ግጭት ቤት ንብረታቸውን ጥለው የሸሹና በመጠለያ ጣብያ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮች በከፋ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገለፁ።

በዚሁ አካባቢ ያሉና ዘንድሮ በክልልም ሆነ በሀገርቀፍ ደረጃ ብሄራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችም እስካሁን የፈተና ፎርም አልሞሉም ይላሉ - የማዕከላዊ ጎንደር የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ።

የክልሉ የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት በበኩሉ በክልሉ ከ91ሺ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም በቢልየን የሚቆጠር ብር ያስፈልጋል ይህንን ገንዘብ የሚያሰባስብ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል።

በተለይ በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች ያሉ ተፈናቃዮችን በሁለት ወራት ውስጥ ወደ ቀያቸው ለመመለስ መንግሥት ቁሳቁሶችን እያሟላ ሲሆን የተማሪዎችን ችግርም ለመፍታት ዕቅድ ተይዟል ብለዋል የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ግጭት የተፈናቀሉ በከፋ ችግር ውስጥ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:38 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG