በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ


የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ስርዓተ ቀብር
የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ስርዓተ ቀብር

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር መስራች ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ስርዓተ ቀብር፣ ዛሬ በትውልድ ቦታቸው መርሃዊ ከተማ ተፈፀመ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር መስራች ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ስርዓተ ቀብር፣ ዛሬ በትውልድ ቦታቸው መርሃዊ ከተማ በርካታ አድናቂዎቻቸውና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በማኅደረ ስብሃት ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን በጀግና የአቀባበር ሥርዓት ተፈፀመ።

ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ሶማልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ የሚጠበቅባቸውን ወታደራዊ ግዳጅ በብቃት በመወጣት ሀገርን ከወራሪ ኃይል የታደጉ ሲሆን የሀገሪቱን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን የተሸለሙ ናቸው፡፡

ኮ/ል ታደሰ በኢትዮጵያ አየር ኃይል በነበራቸው ቆይታ በርካታ የበረራ ባለሙያዎችን ያፈሩ የሀገር ባለውለታም ነበሩ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG