በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራና በትግራይ ክልሎች የወሰን ውዝግብ


የፌደፌሽን ም/ቤት በክልሎች መካከል የሚፈጠረውን የወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ሲገባው በአማራ ክልል በህጋዊ መንገድ የቀረበ የማንነት ጥያቄ የለም ብሎ መደምደሙ በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል አላስፈላጊ ውዝግብ እንዲፈጠር እያደረገ ነው ሲሉ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የፕሬዚዳንቱ የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪ አቶ መርሃፅድቅ መኮነን ተናገሩ።

የፌደፌሽን ም/ቤት በክልሎች መካከል የሚፈጠረውን የወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ሲገባው በአማራ ክልል በህጋዊ መንገድ የቀረበ የማንነት ጥያቄ የለም ብሎ መደምደሙ በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል አላስፈላጊ ውዝግብ እንዲፈጠር እያደረገ ነው ሲሉ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የፕሬዚዳንቱ የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪ አቶ መርሃፅድቅ መኮነን ተናገሩ። አቶ መርሃፅድቅ አያይዘውም አሁን የተቋቋመው የአስተዳደር የወሰንና የማንነት ኮሚሽን ገለልተኛ ሆኖ ያጠናውን የውሳኔ ሃሳብ ስልጣን ላለው አካልና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርባል ።

የውሳኔ ሃሳቡን ሥልጣን ያለው አካል የማያስፈፅም ከሆነ በፊደራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት መፍትሄ እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል። የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በቅርቡ በአማራ ክልል በህጋዊ መንገድ የቀረበ የማንነት ጥያቄ የለም ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአማራና በትግራይ ክልሎች የወሰን ውዝግብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:57 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG