የዩናይትድ ስቴስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የዓለምን ትኩረት እንደሳበ ቢታመንም አፍሪካ ቀንድ ውስጥ በምትገኝ አገርም ወቅቱ የፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚካሄድበት ነው - በሶማሊያ፡፡
የመንና ጅቡቲ ውስጥ የተቀሰቀሰው የስደተኛ እና የፍልሰተኞች ቀውስ በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ከባድ እንድምታ እየፈጠረ ነው ሲል ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት/አይኦኤም/ አስጠነቀቀ።
በኢትዮጵያ የኦሮምያ ክልል ሲካሄድ በቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት የውጭ ሀገር ዜጎች ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ድርጊቱ የሀገሪቱን የምጣኔ ሃብት ዕድገት ሊያሰናክል ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። ተንታኞች ግን የምጣኔ ሃብት ዕድገቱ እንዲቀጥል አንዱ ቁልፍ ርምጃ የተቃዋሚዎችን ብሶት አድምጦ መፍትሄ መስጠት መሆኑን ይመክራሉ።
የአፍሪካውያን አሜሪካውያን ታሪክና ባህል ብሔራዊ ቤተ መዘክር በመጀመሪያው አፍሪካዊ አሜሪካዊ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ተመርቆ ተከፍቷል።
በኢትዮጵያ ደቡብ ህዝቦች ክልል ሆሳዕና በሚገኝ እስር ቤት ካለፈው ዕሁድ ጀምሮ የመንግስት ሓይሎች በእስረኞች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ከእስረኞች አንዱ ገለጹ።
በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ትናንት ማክሰኞ ማምሻው ላይ ከመንግሥት ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። የአንደኛው ወጣት ወላጅ እናት እኔንም የልጄ አስከሬን ላይ ጥለው ደበደቡኝ ብለዋል።
በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ ትናንት ሰኞ ማታ ሁለት ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ሓይሎች መገደላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች እና የሆስፒታል ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርነት ጊዚያቸውን የሚያጠናቅቁት ፓትሪሺያ ሃስላክ ትናንት በኤምባሲው የስንብት ንግግር አድርገዋል።
በኒውዮርክ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ረፋዱ ላይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት ደጃፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
ሂላሪ ክሊንተን የተዘጉ በሮችን ያስከፈተ የትግልና የአገልግሎት ህይወት
የሬፖብሊካን ፓርቲ ጉባዔ በሚካሄድበት ክሊቭላንድ ከታዩት የተቃውሞ ትእይንቶቹ በአንደኛው ላይ የአሜሪካ ባንደራ መቃጠሉን ተከትሎ ፖሊስ አንዳንድ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል።
ወይዘሮ ቅድስት ገረመው በኣሜሪካ ዋና ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የኣፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በበጎ ፈቃደኛ ኮሚሽነርነት ያገለግላሉ።
ሰኞ ማታ የሬፖብሊካን ፓርቲ አባላት ጉባዔአቸውን በከፈቱት አዳራሽ ውጪ እና ውስጥ ተቃውሞ እየተሰማ በነበረበት በከፍተኛ ሁካታ መሃል ነበር።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም መልዕክተኛ የሆነችው አሜሪካዊት ተዋናይት ቻርሊዝ ቴሮን እኤአ 2030 ዓ.ም የመጨረሻው ዓመታዊ ዓለምአቀፍ የኤድስ ጉባኤ ይሁን ስትል ጥሪ አቀረበች።
የአፍሪካ ህብረት ኮምሺን ሊቀመንበር መረጣው ሂደት እንዲቆይ ተደረገ: ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከቀረቡት ዕጩዎችን አንዳቸውም ሁለት ሶስተኛ አብላጫ ድምጽ ባለማግኘታቸው መሆኑን ታውቋል።
ባለፈው ሳምንት ሰኞ የተከበረው የአሜሪካ የነፃነት ቀን በየዓመቱ እኤአ ሃምሌ 4 ቀን አሜሪካ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷዋን ያወጀችበት መታሰቢያ በዓል በወታደራዊ ባንዶች እና በርችት ተኩስ ያከበራል።
በሉዊዚያና እና ሚኒሶታ ክፍላተ ሀገር ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን ወንዶች በፖሊሶች ጥይት የተገደሉበት እንዲሁም በቴክሳስ ዳላስ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አምስት ፖሊሶች በጥይት የተገደሉባት ሳምንት ነው- በዩናይትድ ስቴትስ።
ልጆቻችን ባህላቸውን ታሪካቸውን እና ቋንቋቸውን በአጠቃላይ የመጡበትን ሲያውቁ በራሳቸው ይኮራሉ።
ተጨማሪ ይጫኑ