ዋሺንግተን —
መስሪያ ቤቱ ለአፍሪካውያን የከተማዋ ነዋሪዎች የጤና የትምህርት የስራ ዕድል ወዘተ በሚገባ መዳረሱን ለማረጋገጥ የቆመ ሲሆን የመብት አለመከበርን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮች ለሚደርሱባቸው የማህበረሰብ አባላት ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ይሰራል።
ታዲያ ወይዘሮ ቅድስት የዲሲ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ ሳለ በአገልግሎታችን ለመጠቀም የሚመጡት ቁጥር ግን እጅግ አናሳ ነው በማለት ይቆጫሉ። “እባካችሁ ኑና ተገልገሉ ተሳተፉ” በማለትም ይማጸናሉ።
በቅርቡ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ የአፍሪካ ክፍል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫና የአፍሪካውያን ተሳትፎን በሚመለከት ባሰናዳው ውይይት ላይ የተገኙት ወይዘሮ ቅድስት ስለ ምርጫ ተሳትፎ አስፈላጊነት እና የዲሲ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ስለሚሰጠው አገልግሎት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።