ዋሺንግተን ዲሲ —
ሶማሊያ በመጭው ኅዳር ወር ማብቂያ ላይ ፕሬዘዳንቷንና የምክር ቤት አባሎቿን ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።
እስካሁን አጠቃላይ የምርጫዎቹ ሂደት መልካም መሆኑን፣ የምክር ቤት አባል የሆኑት አብዲዋሊ ቋንያሬ ገልጸዋል።
“በየትኛውም ዓለም በሰለጠኑትም ቢሆን ምርጫ በሚካሄበት ጊዜ ቅሬታ የሚያሰሙና ምርጫው ትክክል አይደለም የሚሉ ወገኖች መኖራቸው የሚታወቅ ቢሆንም የእስከ አሁኑ የእኛ አካሄድ ግን ሰላማዊ ነው” ሲሉ የምክር ቤት አባል ቋንያሬ አክለው ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።