በሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው በሶማሊያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ባለፈው ሰኞ ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል ።
ወደ ሶሪያ ተጉዘው እስላማዊ መንግስት ነኝ ባዩን ቡድን ለመቀላቀል በማሴር የተከሰሱት የዩናይትድ ስቴትስ ሚኔሶታ ነዋሪዎች ሶማሊያዊ አሜሪካውያን የፍርድ ሂደት ቀጥሏል።
የዓለም ዋንጫ ለመመልከት የተሰበሰቡ ሰባ ስድስት ሰዎችን ከገደሉት የሽብርተኛ ጥቃቶች በተያያዘ የተከሰሱ ሰባት ሰዎች ላይ የጥፋተኘት ብይን ሰጠ።
ናይጄሪያ ውስጥ ተጠርጣሪ የጽንፈኛ እስላማዊው ቦኮ ሃራም አባላት በሚታሰሩበት ወታደራዊ የእስር ማዕከል በከበደ ጉስቁልና የነበሩ ቁጥራቸው ውደ አስራ ሁለት የሚጠጋ ልጆች፣ ህጻናትም ጭምር በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት መሞታቸውን አምነስቲ ኢንተርናሺናል አስታወቀ። ለሰብአዊ መብቶች ከበሬታ ተሙጋቹ ድርጅት ናይጄሪያን በተደጋጋሚ ሲከሳት ቆይቷል። የናይጄሪያ መንግስት በበኩሉ ክሶቹን ያስተባብላል። ቦኮ ሃራምን በስኬት ድል እየመታሁ ነኝ ይላል።
በግጭት እየታመሰች ባለችው በቡሩንዲ ሰላም ለማምጣት የክልሉ ሀገሮች አዲሱ ሸምጋይ እንዲሆኑ የቀድሞ የታንዛኒያ ፕሬዚደንት ቤንጃሚን ምካፓን መሰየማቸው የሰላም ሂደቱን ያንቀሳቅሰዋል የሚል ተስፋ ተጥሎበት ነበር ። ይሁን እንጂ ሰኞ ታንዜንያዋ አሩሻ ከተማ ሊካሄድ የነበረው እስከወሩ መጨረሻ ገደማ እንዲዘገይ ተደርጓል። በዚህ መሃልም በሀገሪቱ እስሩ፣ የእጅ ቦምብ ጥቃቶች እና ግድያዎቹ እንደቀጠሉ በመሆኑ የሰላም ንግግር ጥረቶችን ይበልጡን እየተወሳሰበ መጥቷል።
የሱዳን መንግስት የሃገሪቱ ዕለታዊ ጋዜጦች በተወሰኑ የፕሬስ ተቋማት ስር እንዲዋሃዱ በታለመው ዕቅዱ ዙሪያ ለመነጋገር የተጠራ የጋዜጠኞች ስብሰባ እንዳይካሄድ ከለከለ ተብሎ የቀረበውን ውንጀላ አስተባበለ።
ከዚያ ወዲህ ሃምሳ ሰባቱ ልጃገረዶች ከጠላፊዎቻቸው እጅ ያመለጡ ሲሆን ሁለት መቶ አስራ ዘጠኙ እስካሁን አልተገኙም። ቦኮ ሃራም ከሁለት መቶ በላይ ልጃገረዶችን በጠለፈ በሁለት ዓመቱ ብቅ ያለ አዲስ ቪዲዮ ለወላጆቻቸው በህይወት አሉ የሚያሰኝ ተስፋ ፈንጥቋል።
ስማርትፎን ስልኮች ያሏቸው ሰዎች በሀገሪቱ ብቸኛው በሆነው በመንግስቱ ኢቲዮቴሌኮም የፌስቡክም ሆነ የትዊተር መልዕክት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን ወሊሶ ከተማ የዩኒቨርስቲ መምህር ስዮም ተሾመ መናገራቸውን ብሉምበርግ ጠቅሷል።
የአለም አቀፍ ውንጀል ፍርድ ቤት አይ ሲ ሲ (ICC) በኬንያ ምክትል ፕሬዚደንት እና በአንድ የሀገር ውስጥ ራዲዮ ጣቢያ ስራ አስኪያጅ እ.አ.አ. በ 2007 ዓመተ ምህረት ከተካሄደው ምርጫ ተከትሎ በተፈጸሙ ወንጀሎች ሚና ተጫውተዋል ተብለው የቀረቡባቸውን ክሶች ሰርዟል። ይህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሀገሪቱ በሚቀጥለው ዓመት ምርጫዎች ላይ ከፍተኛ እንድምታ እንደሚኖረውም ተገልጿል።
ከቀረቡት ዘግናኝ ውንጀላዎች መካከል ቢያንስ ሶስት ልጃገረዶች የፍረንሳይ ወታደሮች በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ይዘውን ከውሻ ጋር ወሲብ ግንኙነት እንድንፈጽም አድርገውናል ሲሉ ለአንድ የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብት ባለስልጣን ተናግረዋል።
ድርጊቱ ፒዮንግያንግ ከደቡብ ኮሪያና ከአጋሮቹዋ ጋር ያላትን ውጥረት የሚያባባስ መሆኑ ተመልክቷል።
ሊቀመንበሩ የቀድሞ የቦትስዋና ፕሬዚደንት ፌስቱስ ሞጋዬ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶች ቢኖሩም በቅርብ ጊዜ የተከናወኑ ርምጃዎች የሽግግሩ መንግስት ምስረታ ሩቅ እንደማይሆን ኣመላክተዋል ብለዋል።
ፕሬዚደንት ሙሴቬኒ ስድሳ ከመቶውን ድምጽ ተቃዋሚ መሪው ተፎካካሪያቸው ኪዛ ቢሲጂ ደግሞ ሰላሳ ነጥብ አምስት ከመቶ ድምጽ እንዳገኙ ነው የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ያስታውቀው።
የደቡብ ሱዳን የአማጽያን መሪ ሪያክ ማቻር የ28 ከፍላተ-ሀገር ዕቅድ በመቃወም ጉዳያቸውን ለአፍሪካ ህብረት ለማቅረብ ወስነዋል።
ከክረምት በረዶ ሁኔታ በተያያዘ ምክንያት ቢያንስ ሃያ አራት ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።
የሰላም ስምምነቱ የተደረሰው በሊቢያ ተቀናቃኝ መንግሥታት መካከል ብዙ ዙር ድርድር ከተካሄደ በኋላ መሆኑ ይታወሳል።
አራት አጥፍቶ ጠፊዎች ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አምስት ሰዎች መግደላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል አንድ የከተማዋ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
ሼክ ሶሞው የተባሉ ዕማኝ፡- "ብዙ ሰዎች ወድቀው ድረሱልን እያሉ ሲጮሁ ይሰማ ነበር። አጥቂዎቹ ሆቴሉን እንዳለ ሲይዙት እግሬ እውጪኝ ብየ አመለጥኩ"
ለአፍሪካ ቀንድ ግዙፍ ርዳታ ለጋሾች አንዱ የሆነው የአውሮፓ ህብረት እአአ ከ 2011 ዓ.ም.ወዲህ ከአንድ ቢሊዮን ዩሮ በላይ ለሰብዓዊ ርዳታ ለግሷል።
ተጨማሪ ይጫኑ