በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ለሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት ዕድገት የተቃዋሚዎች ብሶት መደመጥ አለበት" ተንታኞች


በተቃውሞው ወቅት በሰበታ ከተማ ከተቃጠሉት የአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ማምረቻ መኪና
በተቃውሞው ወቅት በሰበታ ከተማ ከተቃጠሉት የአርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ማምረቻ መኪና

በኢትዮጵያ የኦሮምያ ክልል ሲካሄድ በቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት የውጭ ሀገር ዜጎች ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ድርጊቱ የሀገሪቱን የምጣኔ ሃብት ዕድገት ሊያሰናክል ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። ተንታኞች ግን የምጣኔ ሃብት ዕድገቱ እንዲቀጥል አንዱ ቁልፍ ርምጃ የተቃዋሚዎችን ብሶት አድምጦ መፍትሄ መስጠት መሆኑን ይመክራሉ።

ጽ/ቤቱ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ካሊፎርኒያ የሆነው የፖሊሲ ጥናትና ትንተና ተቋም ኦክላንድ ኢንስቲሲዩት ዋና ስራ አስኪያጅ አኑራድሃ ሚታል "ትኩረትን አኢኮኖሚ ግንባታ ላይ በቻ አድርጎ ባላሁለት አሀዝ እያሉ ማውራቱ ብቻውን አይጠቅምም" ብለዋል።

አያይዘውም "የሕዝቡን ዴሞክራሲ በመንፈግ፣ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶቹን በመከልከል ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አያዛልቅም ይፈርሳል። መንግስት ይሄን ማጤን አለበት።" ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

"ለሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት ዕድገት የተቃዋሚዎች ብሶት መደመጥ አለበት"ተንታኞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:19 0:00

የእንግሊዘኛውን ሪፖርት ለማግኘት ተጨማሪን ይጫኑ

XS
SM
MD
LG