በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቀንድ ፍልሰተኞች ቀውስ በየመንና በጅቡቲ


ህገወጥ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያውያን - በየመን ቦርደር
ህገወጥ ፍልሰተኛ ኢትዮጵያውያን - በየመን ቦርደር

የመንና ጅቡቲ ውስጥ የተቀሰቀሰው የስደተኛ እና የፍልሰተኞች ቀውስ በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ከባድ እንድምታ እየፈጠረ ነው ሲል ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት/አይኦኤም/ አስጠነቀቀ።

በየወሩ ቁጥራቸው አስር ሺህ የሚደርስ ፍልሰተኞች የሚበዙት ኢትዮጵያውያን በከባድ ሃሩር በሚንገበገበው በረሃ ረጅም ጉዞ ጅቡቲ ድንበር አቋርጠው ይገባሉ።

ከዚያም ስራ ፍለጋ በግጭት በምትታመሰው በየመን በኩል አድርገው ወደ ሳውዲ አረቢያ ይጓዛሉ።

የሚበዙት ወጣት ወንዶች ሲሆኑ ወደ ሰላሳ ከመቶው ብቻቸውን ያሉ ልጆች ናቸው።

የአስራ ኣንድ ዓመት ትናንሽ ልጆችም አሉባቸው። ሴቶችና ህጻናት በጣም ጥቂት መሆናቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት/አይኦኤም/ አስረድቱዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

የአፍሪካ ቀንድ ፍልሰተኞች ቀውስ በየመንና በጅቡቲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:22 0:00

XS
SM
MD
LG