በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ነቀምት ውስጥ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ


ፋይል- ነቀምት ከተማ
ፋይል- ነቀምት ከተማ

በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ ትናንት ሰኞ ማታ ሁለት ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ሓይሎች መገደላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች እና የሆስፒታል ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

እነኚህ አቢሳ ዋቅጂራ እና መሃመድ ዑስማን የተባሉት ሁለቱ ሰዎች ጭንቅላታቸው ላይ በደረሰባቸው ከባድ ጉዳት ምክንያት መሞታቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

“ትናንት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ። አንደኛው የነቀምት ከተማ ነዋሪ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የትምህርት ደረጃውን ለማሻሻል የክረምት ኮርስ ሊከታተል የመጣ ነው። እነዚህ ሰዎች የተገደሉት በአጋዚ ጦር አባላት ተመትተው ነው። እስከሬናቸው ወደነቀምቴ ሆስፒታል ተወስዱዋል።”
የነቀምት ከተማ ነዋሪዎች

ሁለቱ ሰዎች በምን ሳቢያ ሕይወታቸው ላይ ይህ አደጋ ሊደርስ እንደቻለ የተጠየቁት ነዋሪዎቹ በከተማዋ ሦሥት ቦታዎች ቦምብ ፈንድቶ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ነው ብለዋል። ቦምብ ከፈነዳባቸው ቦታዎች አንዱ ዜሮ ሰባት ቀበሌ በሚባለውና አድማ በታኝ ሃይል የሰፈረበት አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል።

በነቀምቴ ሆስፒታል የሰዎቹን መሞት ያረጋገጡት ዶክተር በቃና ተፈሪ በበኩላቸው እንዲህ ብለዋል።

“ ማታ ኣዳሪ ነበርኩ። ሰዎቹ መሞታቸውን ጽፌ ስማቸውን እንዲሞሉ ለተረኞች ሰጥቼ ወጣሁ። ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት በኃላ ነው አስከሬኖቹ ሆስፒታል የደረሱት ። ያመጡዋቸውም ፖሊሶች ናቸው። ጭንቅላታቸው ላይ ክፉኛ ተመተው ነው ሁለቱም ህይወታቸው ያለፈው።’
ዶ/ር በቃና ተፈሪ

በአሁኑ ጊዜ በነቀምቴ ከተማ ከመንግሥት መስሪያ ቤቶች በስተቀር ከትናንሽ የሻይ ቤቶች አንስቶ እስከ ትላልቅ የንግድ ድርጅቶች ዝግ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል ።

ከነዋሪዎችና ከሆስፒታሉ ያገኝነውን መረጃ ይዘን ከሚመለከታቸው የመንግስት ኣካላት ስለጉዳዩ በስልክ ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ነቀምት ውስጥ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:24 0:00

XS
SM
MD
LG