በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሆሳዕና እስረኞች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ


በኢትዮጵያ ደቡብ ህዝቦች ክልል ሆሳዕና በሚገኝ እስር ቤት ካለፈው ዕሁድ ጀምሮ የመንግስት ሓይሎች በእስረኞች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ከእስረኞች አንዱ ገለጹ።

ታሳሪዎቹ “ የመንግስት ሓይሎች ክፍላችን ቆልፈውብን ጥይትና አስለቃሽ ጭስም ተኩሰው ጉዳት አድርሰዋል” ብለዋል ። ስድስት የሚሆኑ የቆሰሉ እስረኞች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንም ገልጸዋል።

የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሃያ የሚሆኑ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል መወሰዳቸውን እና የሞቱ ሊኖሩ እንደሚችሉ መረጃ እንደደረሳቸው ገልጸዋል።

ዛሬም በእስር ቤቱ ውጥረት መኖሩን፡ እስረኛው ከማረሚያ ቤቱ የሚሰጠውን ምግብ፡ ውሃ መከልከሉን እና ቤተሰብም ስንቅ ማቀበልም ሆነ መጎብኘት እንዳልተፈቀደ ገልጸውልናል።

ይህ ሁኔታ የተቀሰቀሰው የጥበቃ ሓይሎች እስረኛውን ወትሮ የሚፈቀድለትን ስልክና መደወያ ሲም ካርድ አምጡ ብለው መንጠቅና መፈተሽ ሲጀምሩ መሆኑን ፕሮፌሰር በየነ አክለው ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የሆሳዕና እስረኞች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:38 0:00

XS
SM
MD
LG