ዋሺንግተን ዲሲ —
የኬንያ ምርጫ ስምንት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ሲገለፅ የምርጫ ኮምሽኑ ሂደቱን እንዴት ማከናወን ይገባዋል በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ንትርኩ ከወዲሁ ተጧጡፉል።
የኮሚሽኑ አባላት ሥራቸውን ይልቀቁ ተብሎ ለበርካታ ሳምንታት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሲካሄድ ከቆየ በኋላ ባለፈው መስከረም ወር በሀገሪቱ ፓርላማ የሁለቱም ጎራዎች አባላት የምርጫ አፈፃፀም ለውጥ ሕጎች አሳልፈዋል።
መሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ዘግቧል ቆንጂት ታየ ታቀርበዋለች፡፡
ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡