በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ በጄነቫ


የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ በጄነቫ
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ በጄነቫ

የመሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ የተመረኮዘው የዓለም ሠላምና መረጋጋት “ደንታ ቢስ የፖለቲካ ጥቅም አግበስባሶች” በሚባሉት አደጋ ተደቅኖባቸዋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዜይድ ራዓድ አል ሁሴን አስጠነቀቁ።

የመሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ የተመረኮዘው የዓለም ሠላምና መረጋጋት “ደንታ ቢስ የፖለቲካ ጥቅም አግበስባሶች” በሚባሉት አደጋ ተደቅኖባቸዋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዜይድ ራዓድ አል ሁሴን አስጠነቀቁ ።

ኮሚሽነሩ ይህን ያሰጠነቀቁት ጄነቫ ውስጥ በተጀመረው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ መክፈቻ ላይ ነው።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ወዲህ የዓለምን ስርዓት ለማረጋጋት የተደረጉ በርካታ ክንዋኔዎች በአሁኑ ወቅት እያደገ በመጣው የተራውን ሕዝብ ብሶትና ሥጋት የፖለቲካ መጠቀሚያ የማድረግ ተግባር የመፈራረስ አደጋ ተደቅኖባቸዋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሺነር ዜይድ ራአድ አል ሁሴን አስጠንቅቀዋል።

ከአውዳሚው የዓለም ጦርነት በተከተሉት ሰባ ዓመታት በበርካታ የዓለም አካባቢዎች ዘላቂ ሠላምና ልማት ዕውን ሊሆን የቻለው በመንግሥታቱ ድርጅት ቻርተርና በሌሎችም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውሎች የተደነገጉት መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች በመከበራቸው ነው ብለዋል።

የፖለቲካ መሪዎች በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ላይ ለሚያካሂዱዋቸው የክፋት ዘመቻዎች ወይም ደግሞ ለእነዚህ መብቶች ከቆሙ ውሎች እንወጣለን ብለው ለሚያሰሙት ዛቻ ከተንበረከክን ዓለማችን ከባድ ጉዳት ያገኛታል ሲሉ ከፍተኛው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር አስጠንቅቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ በጄነቫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:55 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG