በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ሦስተኛ ሆናለች


ሲፒጄ
ሲፒጄ

ዋና መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ(CPJ) ዓመታዊ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችን ቁጥር ቀምሮ ይፋ በሚያደርግበት ዓመታዊ ሪፖርቱ በዚህ ወር በሚጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ 259 ጋዜጠኞች ታስረው እንደሚገኙ አስታውቋል። በዚህ ሪፖርቱ ከአፍሪካ ግብጽ 25 ጋዜጠኞችን በማሰር 1ኛ፣ ኤርትራ 17 ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛና ኢትዮጵያ 16 ጋዜጠኞችን በማሰር ሦስተኛ ሀገር ተብላለች።

የሲ.ፒ. ጄ የምስራቅ አፍሪካ ተጠሪ ሙሬቲ ሙቲጋን ለአሜሪካ ድምጽ ሲናገሩ በዓለም ዙሪያ ጋዜጠኞችን ማሳደድ እና ማሰር እየተባባሰ መምጣቱ ሲፒጄን እጅግ እያሳሰበው እንደሆነ ተናግረዋል። በተለይ እንደቱርክ ባሉት ሀገሮች በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እጅግ እየተባባሰ እንደመጣ ሪፖርቱን ጠቅሰው ተጠሪው ተናግረዋል።

ሙረቲ አያይዘው አፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለጋዜጠኞች በአንደኛ ደረጃ ክፉ ሀገር ኤርትራ መሆኗን ጠቅሰው ለዚህም ምክንያት ነው ብለው ያቀረቡት ጋዜጠኞች ቤተሰቦቻቸውና በወዳጅ ዘመዶቻቸው መጎብኘት አለመቻላቸውን ነው። ቤተሰብና ዘመዶቻቸው እስረኞቹ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ሳያውቁ ከዐስር ዓመታታ በላይ የታሰሩ አሉ ብለዋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ በሁለተኛ ደረጃ የከፋች ሀገር ተብላለች። በአጠቃላይ አፍሪካ ደግሞ ግብጽ 25 ጋዜጠኞችን በማሰር አንደኛ አፋኝ ሆናለች።

ቆንጅት ታዬ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ሦስተኛ ሆናለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:28 0:00

XS
SM
MD
LG