“የአገር ደህንነት ሚኒስትር ጆን ኬሊ በጣም ጥቂት ችግሮች በስተቀር ሁሉ ነገር በጥሩ ሁኔት እየሄደ ነው ብለውኛል” ሲሉ፤ ዛሬ ፕሬዚደንት ትረምፕ በተከታታይ በትዊተር ባስተላልለፉዋቸው መልዕክቶች ገልጸዋል።
አውሮፕላን ጣቢያዎች ላይ የተፈጠረው ትልቁ ችግር በተፈጠረው ዴልታ ኣየር መንገድ ላይ የደረሰው የኮፒዩተር ብልሽት፥ በተቃዋሚ ሰልፈኞችና የኒውዮርኩ ሴኔተር ቸክ ሹመር ዕንባ ምክንያት ነው ብለዋል ፕሬዚደንቱ።
ሴናተሩ ትላናት እሁድ ለሚስተር ትረምፕ የማስፈጸሚያ ትዕዛዙን እንዲቀለብሱ ተማጽኖ ባሰሙበት ሰዓት እንባ ሲተናነቃቸው ታይተዋል።
ሚስተር ትረምፕ ብለፈው አርብ የፈረሙት የኢሚግሬሺን ማስፈጸመሚያ ትዕዛዝ ለአንድ መቶ ሃያ ቀናት ስደተኛ መቀበል እንዲቋረጥ ከኢራቅ ከኢራን ከሶሪያ ከሶማሊያ ከሱዳን ከሊቢያ እና ከየመን የሆኑ ሰዎች እንዳይገቡ የሶስት ወር እግድ ያዛል።
የዚህ ትዕዛዝ አፈጻጸም ታዲያ በተለይ በበዩናይትድ ስቴትስ አውሮፕላን ጣቢያዎች በፈጠረው መደነጋገር ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ግሪን ካርድ ያላቸው አንዳንድ መንገደኞች ጭምር ለተጨማሪ ጥያቄ የተወሰዱበት ሁኔታም ነበር።
በፕሬዚደንቱ የዕገዳ ትዕዛዝ ዓላማ ከተደረጉት ሀገሮች የተነሱ አንዳንድ መንገደኞች ወደ አሜሪካ በሚመመቱ በረራዎች እንዳይሳፈሩ የተከለከሉም አሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ