በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የዚህ ድል ባለቤት የሶማልያ ህዝብ ነው" አዲሱ የሶማልያ ፕሬዚዳንት


አዲሱ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድን
አዲሱ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድን

ሶማልያ አዲስ ፕሬዚዳንት መርጣለች፤ ትናንት ነው የሶማሊያ ፓርላማ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድን የመረጣቸው። አዲሱ ፕሬዚደንት የተመረጡት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ መሃሙድን 184 ለ97 በሆነ ድምፅ ብልጫ አሸንፈዋቸው፡፡

ሶማልያ አዲስ ፕሬዚዳንት መርጣለች፤ ትናንት ነው የሶማሊያ ፓርላማ በሁለተኛ ዙር ምርጫ ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድን የመረጣቸው። አዲሱ ፕሬዚደንት የተመረጡት የቀድሞውን ፕሬዚደንት ሃሰን ሼክ መሃሙድን 184 ለ97 በሆነ ድምፅ ብልጫ አሸንፈዋቸው፡፡

ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ በምርጫው ማሸነፋቸው ይፋ ከተደረገ በኋላ ወዲያውኑ ቃለ መሃላቸውን ፈፅመዋል።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ባደረጉት አጭር ንግግር

“የዚህ ድል ባለቤት የሶማልያ ህዝብ ነው። ይህ ድል አንድነቷ የተጠበቀ፣ ሰላማዊና የተረጋጋች ሶማልያን የመገንባት ሥራ የሚጀመርበት ነው። ለዲሞክራሲና የፀረ - ሙስና ዘመቻም የምንያያዝበት ነው” ብለዋል።

አስረካቢው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሐመድም ትናንት ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለተተኪያቸው መልካም ምኞት በማስተላለፋቸው አድናቆትን አትርፈዋል።

ያ ሁሉ በጎ ጎን ሆኖ ሳለ ሶማልያ አሁንም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ አንድ ሰው አንድ ድምፅ ምርጫ የማካሄድ ግቡዋ ጋ አልደረሰችም። የፀጥታው ጉዳይም አሁንም ትልቅ ፈተናዋ ነው። ባለፈው ዓመት የፓርላማ አባላት በጎሳ መሪዎችና በክልል ተወካዮች መመረጥ ነበረባቸው። ፕሬዚደንታዊ ምርጫውን ጨምሮ የምርጫዎቹ ሂደት ድምፅ በሰፊው በገንዘብ ተቸብችቦበታል የሚሉ ውንጀላዎች አጥልተውበታል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“የዚህ ድል ባለቤት የሶማልያ ህዝብ ነው" አዲሱ የሶማልያ ፕሬዚዳንት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:03 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG