በቅርቡ በጋምቤላ ከተማ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች ስድስት ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች ከአሥራ አምስት በላይ መቁሰላቸው ታውቋል።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሴቶች ላይ በስፋት ለሚደርሰው ወሲባዊ ጥቃትና ድፍረት የሀገሪቱ መንግሥት የመፍትኄ ዕርምጃ አልወሰደም ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች ወነጀሉ።
የአዲስ ዓመት በዓል በስደት ላይ ባሉ ወገኖች ዘንድ እንዴት ተከበረ?
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ትናንት ሰኞ ለአፍሪካ ሃገሮች ስድሳ ቢሊዮን ዶላር መደቡ። ድኅነት ጠና ላለባቸው ሃገሮች ደግሞ የተወሰነውን ዕዳ ሰርዘውላቸዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “ግንቡን እናፍርስ፣ ድልድልዩን እንገንባ” በሚል መሪ ርዕስ በሦስት የአሜሪካ ከተሞች ካሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር የተዋወቁበትን እና የተወያዩበትን ጉዞ አጠናቀው ዛሬ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡
በከፍተኛ የእናቶች ሞት ከሚጠቀሱ የዓለም ሃገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት ። ከአስራ ሰባት ነፍሰ ጡር ሴቶች አንዷ በወሊድ ወቅት ህይወቷን ታጣለች። ይህን ለመታደግ ታዲያ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ርቀው ባሉ ገጠራማ ሥፍራዎች የሚኖሩ ነፍሰጡሮች ለራሳቸውም ሆነ ለሚወለደው ህፃን የጤና እንክብካቤ ማግኘት ወደሚችሉባቸው የጤና ጣቢያዎች አቅራቢያ ጠጋ ብለው የሚቀመጡባቸው ማረፊያ ቤቶች እየተሰናዱላቸው ነው።
በደቡባዊ ኢትዮጵያ ለስምንት መቶ ሺህ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት የሆኑ የጎሣዎች ግጭቶች ሰብዓዊ ቀውሱ እንዲባባስ አድርጓል ሲል ዓለምቀፍ የቀይመስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ጉብኝት አድርገዋል። ከህዝቡ ጋርም ውይይት አድርገዋል።
ዛሬ ጠዋት ግልገል ጊቤ አንድና ግልገል ጊቤ ሁለት ሃይድሮ ኤለክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች መካከል በሚገኝ ትልቅ የኤለክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ በአንድ ትራንስፎርመር ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ወደሌላ እንዳይዛመት ለመከላከልና ለማጥፋት መቻሉ ተገልጿል።
ዛሬ የኢድ አል ፈጥር በዓል በዓለም ዙሪያ እየተከበረ ነው።
ቢያንስ አንድ መቶ ፍልሰተኞችን ይዞ ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ከሶማሊያ ይጓዝ የነበረ የሕገ ወጥ አሸጋጋሪዎች ጀልባ የመን ሲቃረብ ተገልብጦ አርባ ሥድስት ኢትዮጵያውያን ሰጥመው መሞታቸው እና ሌሎች አሥራ ስድሥት የደረሱበት መጥፋቱ ተገለፀ፡፡
የካሜሩን ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት ቦኮ ሃራም በጦር ሰራዊት ሰፈር ላይ ካደረሰው ህይወት ያጠፋ ጥቃት ተከትሎ ከናይጄሪያ ጋር በሚያውስነው ድንበር ላይ የሚኖሩ ማኅበረሠቦች አሁንም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እያሳሰቡ ናቸው።
በአሜሪካ የሲቪል መብቶች ለማስከበር በሚሊዮኖች የተቆጠረ ህዝብ ያንቀሳቀሱት ቄስ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በነፍሰ ገዳይ ጥይት ከተገደሉ ዛሬ ሃምሳ ዓመት ተቆጠረ።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ፓርላማ የዶ/ር አብይ አህመድን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት የማፅደቁን ዜና በደስታ መቀበሉን ገልጿል።
በዚህ ሳምንት የገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡትና የፊታችን ሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት ዶ/ር አብይ አህመድ በሀገሪቱ ሥር የሰደደውን የሰብዓዊ መብት ቀውስ መፍታትን ቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጡት ፅህፈት ቤቱ ለንደን የሆነው የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሺናል አሳሰበ።
ለሴቶች መብት ለአካል ጉዳተኞች መብትና ዕኩልነት ተሟጋች ጠበቃዋ፣ የትነበርሽ በዛሬው ዓለምቀፍ የሴቶች ቀን አንድ ከፍተኛ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
በኢትዮጵያ አፋር ክልል የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የነበሩ አቶ ራሺድ ሳልህ የተባሉ ሰው ለህክምና ወደጅቡቲ ተጉዘው ሲመለሱ የደረሱበት ከጠፋ ሦስት ወር አለፈ።
ቅዳሜ በ1/27/2018 ሜሪላንድ ሲልቨርስ ስፕሪንግ የሚከናወነው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያት የመብት ተሟጋችነት አስተዋፅዖ ታሪክ የሚዘክረው የዶክተር ማይገነት ሽፈራው መጽሐፍ “Struggle From Afar” ይምረቃል፡፡
የእኩልነት መዛባት እና ሊሎችንም ማኅበራዊ ችግሮች ላይ ያተኮሩ የሴቶች ሰልፎች ቅዳሜና እሁድ ዩናይትድ ስቴትስና አውሮፓ ትላልቅ ከተሞች ተካሂደዋል።
ለኢትዮጵያ የመንግሥት ሰራተኛ ሴቶች የሚሰጠው የወሊድ ፈቃድ ሦስት ወር የነበረው አራት ወር እንዲሆን ተራዝሟል።
ተጨማሪ ይጫኑ