ዋሺንግተን ዲሲ —
በአሜሪካ የሲቪል መብቶች ለማስከበር በሚሊዮኖች የተቆጠረ ህዝብ ያንቀሳቀሱት ቄስ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር በነፍሰ ገዳይ ጥይት ከተገደሉ ዛሬ ሃምሳ ዓመት ተቆጠረ።
ኪንግ በሁከት አልባ ትግል ፍልስፍናቸው አማካይነት ዩናይትድ ስቴትስ የሃያኛው ክፍለ ዘመን ሁለት ታላላቅ ህግጋቷን የምትደነግግበት ደረጃ ላይ እንድትደርስ ረድተዋል። አንደኛው የሺህ ዘጠኝ መቶ ስድሳ አራቱ የሲቪል መብቶች ህግ ሲሆን ሌላው የሺህ ዘጠኝ መቶ ስድሳ አምስቱ የመምረጥ መብት ነው።
የቪኦኤው አራሽ አራብሳዲ የኒህን የአሜሪካ ሲቪል መብቶች ንቅናቄ መሪ ታሪክ መለስ ብሎ ይቃኛል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ