በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት ምስረታ በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሊከናወን እንደሚችል ተገለጸ


ፋይል ፎቶ - ሬክ ማቻር በአዲስ አበባ ቃለ-ምልልስ እያካሄዱ እ.አ.አ. 2016
ፋይል ፎቶ - ሬክ ማቻር በአዲስ አበባ ቃለ-ምልልስ እያካሄዱ እ.አ.አ. 2016

ሊቀመንበሩ የቀድሞ የቦትስዋና ፕሬዚደንት ፌስቱስ ሞጋዬ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶች ቢኖሩም በቅርብ ጊዜ የተከናወኑ ርምጃዎች የሽግግሩ መንግስት ምስረታ ሩቅ እንደማይሆን ኣመላክተዋል ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ አንድነት የሽግግር መንግስት ምስረታ በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሊከናወን እንደሚችል የጋራ ቁጥጥር እና ግምገማ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር ተናገሩ።

ሊቀመንበሩ የቀድሞ የቦትስዋና ፕሬዚደንት ፌስቱስ ሞጋዬ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶች ቢኖሩም በቅርብ ጊዜ የተከናወኑ ርምጃዎች የሽግግሩ መንግስት ምስረታ ሩቅ እንደማይሆን አመላክተዋል ብለዋል።

የደቡብ ሱዳን ካርታ
የደቡብ ሱዳን ካርታ

ሁለት መቶ ሰላሳ የሚሆኑ የተቃዋሚው የሱዳን ህዝብ ነጻ አውጭ ንቅናቄ ከፍተኛ መኮንኖች እና ወታደሮች ባለፈው ሳምንት ጁባ ገብተዋል። የተቀሩትን በሙሉ ወደጁባ የሚመልሱ በረራዎች መዘጋጀታቸውን ፌስቱስ ሞጋዬ ጨምረው ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG