በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አስራ አንድ ህጻናት በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ እስር ቤት እንደሞቱ አምነስቲ ኢንተርናሺናል ገለጸ


አንዳንዶቹ ልጆች የሞቱት በኩፍኛ ይዘዋቸው ስለነበር እናም ህክምና ባለማግኘታቸው መሆኑን የከፋ የምግብ የሚጠጡት ውሃና የህክምና ችግርም መኖሩን የዓይን ምስክሮቹ ያስረዳሉ
አንዳንዶቹ ልጆች የሞቱት በኩፍኛ ይዘዋቸው ስለነበር እናም ህክምና ባለማግኘታቸው መሆኑን የከፋ የምግብ የሚጠጡት ውሃና የህክምና ችግርም መኖሩን የዓይን ምስክሮቹ ያስረዳሉ

ናይጄሪያ ውስጥ ተጠርጣሪ የጽንፈኛ እስላማዊው ቦኮ ሃራም አባላት በሚታሰሩበት ወታደራዊ የእስር ማዕከል በከበደ ጉስቁልና የነበሩ ቁጥራቸው ውደ አስራ ሁለት የሚጠጋ ልጆች፣ ህጻናትም ጭምር በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት መሞታቸውን አምነስቲ ኢንተርናሺናል አስታወቀ። ለሰብአዊ መብቶች ከበሬታ ተሙጋቹ ድርጅት ናይጄሪያን በተደጋጋሚ ሲከሳት ቆይቷል። የናይጄሪያ መንግስት በበኩሉ ክሶቹን ያስተባብላል። ቦኮ ሃራምን በስኬት ድል እየመታሁ ነኝ ይላል።

ዕድሜቻው ከስድስት ዓመት በታች የሆኑ አስራ አንድ ልጆች ህጻናትም ጭምር በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ማይዱጉሪ ጊዋ ወታደራዊ ስፈር ባለ እስር ቤት እንደሞቱ አምነስቲ ኢንተርናሺናል ገልጿል።

በእስር ካምፑ ታስረው የነበሩ ሰዎችን በማነጋገር ማስረጃ እንደሰበሰበ ያስታወቀው አምነስቲ ፎቶግራፎችና ቪዲዮውች አቅርቧል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ቃል አቀባይ ሰሎሞን ሳኮ "የሞቱት ልጆች አስከሬን ከመጠን በላይ ከተጨናነቀ የስር ቤቱ ክፍል ሲወጣ አይተዋል። ህጻናቱ ይደርስባቸው የነበረውን እና ለሞት ያበቃቸው የከፋ አያያዝ ተመልክተዋል።" ብለዋል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናሉ ሰሎሞን ሳኮ
የአምነስቲ ኢንተርናሽናሉ ሰሎሞን ሳኮ

በወታደራዊ ካምፑ አቅራቢያ በሚገኝ መካነ መቃብር በቅርቡ የተቆፈሩ ምልክት የሌላቸው የመቃበር ጉድጉዋዶች የሳተላይት ፎቶውችንም አምነስቲ ኢንተርናሺናል በማስረጃነት አቅርቧል።

ምስክሮቹ ለአምነስቲ እንደተናገሩት በሳምንት ሁለት ወይ ሶስት ጊዜ በቆሻሻ መጫኛ መኪናዎች የእስረኞች አስከሬን ወደ መቃብሩ ይወሰዳል። አንዳንዶቹ ልጆች የሞቱት በኩፍኛ ይዘዋቸው ስለነበር እናም ህክምና ባለማግኘታቸው መሆኑን የከፋ የምግብ የሚጠጡት ውሃና የህክምና ችግርም መኖሩን የዓይን ምስክሮቹ አስረድተዋል።

"ዘንድሮ ወደ 150 የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል። አብዛኞቹ እጅግ በከፋ ሁኔታ የነበሩ ወንዶች ናቸው። እንደሰርዲን ተጠጋግተው ስለሚተኙ ትንሽ ገልበጥ ሊሉ እንኳን ፈጽሞ አይችሉም። አንዱ የዓይን ምስክራችን ሁኔታውን፣ 'መጸዳጃ ቤት ውስጥ መኖር ማለት ነው' ሲል ነበር የገለጸው።" ብለዋል ሰሎሞን ሳኮ።

አምነስቲ በዘገባው እንዳለው ባሁኑ ጊዜ በማይዱጉሪው ወታደራዊ ካምፕ አንድ ሺህ ሁለት መቶ እስረኞች ያሉ ሲሆን ቢያንስ አንድ መቶ ሃያው ልጆች ናቸው።

የናይጄሪያ መንግስት የጦር ሃይል ቃል አቀባይ ራቤ አቡባከር
የናይጄሪያ መንግስት የጦር ሃይል ቃል አቀባይ ራቤ አቡባከር

የናይጄሪያ መንግስት ውንጀላውን ያስተባብላል። የጦር ሃይሉ ቃል አቀባይ ራቤ አቡባከር ለአሜሪካ ድምጽ በስልክ በሰጡት ቃል አምነስቲ ወታደራዊ ሰፈሩን ገብቶ እንዲጎበኝ ፈቅደናል ያቀረባቸውን ሃሳቦችም ተግባራዊ አድርገናል ብለዋል።

የአሜሪካ ድምጹ ሄንሪ ሪጅዌል ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጂት አቅርባዋለች፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

አስራ አንድ ህጻናት በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ እስር ቤት እንደሞቱ አምነስቲ ኢንተርናሺናል ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG