በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይስስን ለመቀላቀል በማሴር የተከሰሱ የሚኔሶታ ነዋሪዎች ሶማሊያዊ አሜሪካውያን የፍርድ ሂደት


ጉሌድ አሊ ኦማር፣ ሞሃመድ ፋራህ እና አብዱልራህማን ዱዋድ ለእስልማና መንግስት ቡድን ማቴሪያል ድጋፍ ለመስጠትና ወድ ውጪ ሀገር ተጉዘው ግድያ ለመፈጸም በማሴር ወንጀል ነው የተከሰሱት
ጉሌድ አሊ ኦማር፣ ሞሃመድ ፋራህ እና አብዱልራህማን ዱዋድ ለእስልማና መንግስት ቡድን ማቴሪያል ድጋፍ ለመስጠትና ወድ ውጪ ሀገር ተጉዘው ግድያ ለመፈጸም በማሴር ወንጀል ነው የተከሰሱት

ወደ ሶሪያ ተጉዘው እስላማዊ መንግስት ነኝ ባዩን ቡድን ለመቀላቀል በማሴር የተከሰሱት የዩናይትድ ስቴትስ ሚኔሶታ ነዋሪዎች ሶማሊያዊ አሜሪካውያን የፍርድ ሂደት ቀጥሏል።

ጉሌድ አሊ ኦማር፣ ሞሃመድ ፋራህ እና አብዱልራህማን ዱዋድ ለእስልማና መንግስት ቡድን ማቴሪያል ድጋፍ ለመስጠትና ወድ ውጪ ሀገር ተጉዘው ግድያ ለመፈጸም በማሴር ወንጀል ነው የተከሰሱት ቀድሞ ጓደኛቸው የነበረውን ለፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ የጠቆመባቸው አብዲራህማን በሽር በድብቅ የቀዳው ንግግራቸውና የሰጠው የምስርነት ቃል ባለፈው ሳምንት በዋለው ችሎት ተሰምቷል። ሶስቱ ከሚኒሶታ ወደ ሶሪያ ሄዶ ከአይስሲ የተቀላቀለው ጓደኛቸው ጋር በስካይፕ ሲነጋገሩ ለጉዞአቸው ስለሚያስፈልጋቸው ገንዘብና ሰነድ ሲያወሩ ተቀድተዋል።

እንዳንዱ ጋር በሚተዋወቅበት የሚስጥር ቃላት ሲነጋገሩ ምርሆኑን ጠቋሚው በሺር ለፍርድ ቤቱ ነግሩዋል ። ለምሳሌ በቴፕ ቅጂው ላይ ልጅቷ የሚሉት ፓስፖርት ለማለት ”the hot boys on the block" እነዚያ የሰፈራችን ቆንጆ ወንዶች ልጆች ሲሉ ደግሞ ኤፍ ቢ አይ እየተከታተለን ነው ብለው በሚስጥር ሲነጋገሩ መሆኑን አስረድተዋል።

የተከሳሾች ጠበቃ የኤፍ ቢ አዩን ጠቋሚ ለመስቀለኛ ጥያቄ አቅርበውታል። ስለምንድነው በጓደኞችህ ላይ ልትጠቁም የፈለግከው? አፍዝ አደንግዝ ማሪያዋና ትስብ የለም? ብለው ተይቀውታል።

የአንደኛው ተከሳሽ የጉሌድ ኦማር እናት፣ "ጠቋሚው የተናገረው ውሸት ነው ራሱ እየቆሰቆሰ አንድ ዐመት ሙሉ ያልሆነ ነገር ቀዷቸዋል። አንድ ቀን እውነቱ ይወጣል እግዚእብሄር ይረዳናል" ሲሉ ተደምጠዋል።

የአሜሪካ ድምጽ ሰጋቢ ፋላስቲን ኢማን Falastine Iman የተከሳሾቹ አንዷ የሆኑትን እናት አየን ፈራህ (Ayan Farah)እናት በሚኒያፖሊስ ክፍለ-ሃገር እያነጋገረች
የአሜሪካ ድምጽ ሰጋቢ ፋላስቲን ኢማን Falastine Iman የተከሳሾቹ አንዷ የሆኑትን እናት አየን ፈራህ (Ayan Farah)እናት በሚኒያፖሊስ ክፍለ-ሃገር እያነጋገረች

የሌላኛው ተከሳሽ አየን ፋራህ ሞሀምድም "ጠቋሚምው ቀጣፊ ነው ልጆቻችንን በገንዘብ ሸጠ ስራ የለውም በሚማሩበት ኮሌጅ ቤት እየተከታትለ የሚቀዳቸው ለገንዘብ ብሎ ነው" ሲሉ አማርረዋል።

የክስ ሂደቱን እያዳመጠ ስላለው ከህዝብ የተውጣጣ የፍርድ ሸንጎ የተከሳሹ አብዲራሂም እናት ሲናገሩ "አንድም ሙስሊም አንድም ጥቁር ሰው የሌለብት ሸንጎ ነው ፌደራሉ ምርመራ ቢሮ ብዙ ነገር እየነገራቸው ነው ግን ፍትሃዊ ይሆናሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል። የጠቋሚው የመስቀለኛ ጥያቄ ምርምመራ ሂዳት ቀጥሏል።

ሚኒያፖሊስ ከተማ እያተካሂደ ያለውን የፍርድ ቤት ውሎውን ተከታትላ የአሜሪካ ድምጿ ፋላስቲን ኢማን ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጂት ታዬ አቀርበዋለች።

አይስስን ለመቀላቀል በማሴር የተከሰሱ የሚኔሶታ ነዋሪዎች ሶማሊያዊ አሜሪካውያን የፍርድ ሂደት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG