ዋሽንግተን ዲሲ —
የዑጋንዳ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ባለፈው የካቲት በተካሄድው ምርጫ በድጋሚ መመረጣቸውን የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትናንት አጽድቆታል። ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ተፎካካሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አማማ እምባባዚ ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።
ፕሬዚደንት ሙሴቬኒ ስድሳ ከመቶውን ድምጽ ተቃዋሚ መሪው ተፎካካሪያቸው ኪዛ ቢሲጂ ደግሞ ሰላሳ ነጥብ አምስት ከመቶ ድምጽ እንዳገኙ ነው የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ያስታውቀው።
የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሺኑ የምርጫ ህጎቹን ስላላከበረ ውጤቶቹ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንዲሰርዝ አማማ አኢምባባዚ ጠይቀው ነበር። ሆኖም ፍርድ ቤቱ አንዳንድ የተዛባ አሰራር ቢኖርም የድምጽ ውጤቱን ለመሰረዝ የሚያበቃ አይደለም ብሏል።