በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል €77 ሚሊዮን እንደሚሰጥ አስታወቀ


ለአፍሪካ ቀንድ ግዙፍ ርዳታ ለጋሾች አንዱ የሆነው የአውሮፓ ህብረት እአአ ከ 2011 ዓ.ም.ወዲህ ከአንድ ቢሊዮን ዩሮ በላይ ለሰብዓዊ ርዳታ ለግሷል።

የአውሮፓ ህብረት በአዲሱ የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም. ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል ሰባ ሰባት ሚሊዮን ዩሮ (€77 million) እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ገንዘቡ በአብዛኛው በአጣዳፊ ችግር ላይ ላሉ ማኅበረሰቦች ለምግብ፣ ለጤና፣ ለውሃ፣ ለንጽህና፣ ለመጠለያ እና ለደህንነት ጥበቃና ለትምህርት የሚውል መሆኑ ተገልጿል ።

የአውሮፓ ህብረት ኮምሽን የሰብዓዊ ርዳታ አርማ
የአውሮፓ ህብረት ኮምሽን የሰብዓዊ ርዳታ አርማ

ይህ አዲስ የተመደበው ገንዘብ ህብረቱ ባለፈው 2015 ዓ.ም. መጨረሻ በታህሳስ ወር ከኤል ኒኞ የአየር ሁኔታ ክስተት በተያያዘ ለኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ዩጋንዳ ከመደበው የሰባ ዘጠኝ ሚሊዮን ዩሮ (€79 million)ድጋፍ ተጨመሪ እንደሆነ ታውቋል።

ለአፍሪካ ቀንድ ግዙፍ ርዳታ ለጋሾች አንዱ የሆነው የአውሮፓ ህብረት እአአ ከ 2011 ዓ.ም.ወዲህ ከአንድ ቢሊዮን ዩሮ በላይ ለሰብዓዊ ርዳታ ለግሷል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ሰብዓዊ ርዳታ የሚውል €77ሚሊዮን እንደሚሰጥ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:50 0:00

XS
SM
MD
LG