ዋሽንግተን ዲሲ —
ሶማሊያ ዋና ከተማ ባህር ዳር በሚገኝ አንድ የታወቀ ምግብ ቤት ትናንት ሐሙስ ለደረሰው ጥቃት ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድን አል-ሸባብ ሐላፊነት ወሰደ። ቢያንስ ሃያ ሰዎች ገድለናል ብሉዋል።
ታጣቂዎቹ ሊዶ ቢች ቪው የተባለው ሆቴል በሚገኘው ምግብ ቤት ምሽቱን በከፈቱት ጥቃት ቦምብ ካፈነዱ በሁዋላ በተመጋቢዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል።
ሼክ ሶሞው የተባሉ ዕማኝ፣ አጥቂዎቹ ከወደባህሩ መጥተው ነው ተኩስ የከፈቱት፣ ወደግቢው በር ጋ ሄጄም ተደበቅኩ ብለዋል። ዕማኙ ከዚያ ከባድ ፍንዳታ እንደተሰማም ይገልጻሉ። ከዛም፣ "ብዙ ሰዎች ወድቀው ድረሱልን እያሉ ሲጮሁ ይሰማ ነበር። አጥቂዎቹ ሆቴሉን እንዳለ ሲይዙት እግሬ እውጪኝ ብየ አመለጥኩ" በማለት አክለዋ።
አንድ የሶማሊያ የደህንነት ባለስልጣን ለቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል የጸጥታ ሓይሎች ታጣቂዎቹን ከሆቴሉ መንጥረናል ዋናውን መሪያቸውን ይዘነዋል ብለዋል።
የሶማሊያ የጸጥታ ባለስልጣናት በጥቃቱ ስንት ሰው እንደተገደለ ለመናገር ፈቃደኛ እልሆኑም።
የዜና ዝርዝሩን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።