በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአይ ሲ ሲ ውሳኔ የቀጣዩን የኬኒያ ምርጫ አቅጣጫ ያመለክታል


የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ምክትል ፕሬዚደንት ዊልያም ሩቶ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ በናይሮቢ እ.አ.አ.2014 /ፎቶ - ሮይተርስ/
የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ምክትል ፕሬዚደንት ዊልያም ሩቶ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ በናይሮቢ እ.አ.አ.2014 /ፎቶ - ሮይተርስ/

የአለም አቀፍ ውንጀል ፍርድ ቤት አይ ሲ ሲ (ICC) በኬንያ ምክትል ፕሬዚደንት እና በአንድ የሀገር ውስጥ ራዲዮ ጣቢያ ስራ አስኪያጅ እ.አ.አ. በ 2007 ዓመተ ምህረት ከተካሄደው ምርጫ ተከትሎ በተፈጸሙ ወንጀሎች ሚና ተጫውተዋል ተብለው የቀረቡባቸውን ክሶች ሰርዟል። ይህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሀገሪቱ በሚቀጥለው ዓመት ምርጫዎች ላይ ከፍተኛ እንድምታ እንደሚኖረውም ተገልጿል።

በብዙ ሺዎች የተቆጠሩ የኬንያ ሪፍት ቫሊ ክፍለ ግዛት ነዋሪዎች ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በምክትል ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ ላይ የተመሰረቱት ክሶች እንዲሰረዙ በመወሰኑ ጎዳና ላይ ወጥተው ደስታቸውን ገልጸዋል።

ኮሎኔል ሙዬማ የገዢው የኢዮቤሊዩ ጥምረት ፓርቲ አባል የሆነው ኒው ፎርድ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ናቸው። "በአገር አቀፉም ሆነ በክልላቸው በሪፍት ቫሊ ክፍለ ግዛት አካባቢ በጣም ያጠናክራቸዋል። ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ስራቸውንና ማናቸውንም ውሳኔ ያለስጋት ማድረግ ይችላሉና።" ብለዋል።

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት(ICC)
የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት(ICC)

ኬንያዊ የፖለቲካ ተንታኝ ባራክ ሙሉካ በበኩላቸው በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ሩቶ ለፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩ ከሆነ አሻሚ ባልሆነ መልኩ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣ ላይኖር ይችላል ይላሉ። አክለውም ሲያስረዱ የሚወዳደሩት ከፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታጋር ሊሆን እንደሚችልና ያ ከሆነ ደግሞ በ2007ቱ ምርጫ ወደ ብጥብጥ ያመራውን የብሄረሰቦች ግጭት እንደገና ሊቀሰቅስ እንደሚችል ተንታኙ ያመለክታሉ።

የሪፍት ቫሊ ህዝብ በደምብ ይደግፈኛል ብለው ከደመደሙ 'እንዴ ፕሬዚደንት መሆን ስችል በምክትልነት የምወሰነው ለምንድነው?' ሊሉ ይችላሉ። ያ የፉክክሩን እድማስ ያሰፋዋል።" ብለዋል።

በ2007ቱ ምርጫም ኬንያታና ሩቶ የተሰለፉት በተቃራኒ ጎራ እንደነበር ይታወሳል። ከምርጫው ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ ከ1100 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸውና ስድስት መቶ ሺህ ህዝብ ከመኖሪያው መፈናቀሉ ይታወሳል። አይ ሲ ሲ ICC ኡሁሩ ኬንያታን፣ ዊሊያም ሩቶ እና የራዲዮ ጣቢያ ስራ አስኪያጁን ብጥብጡን በማነሳሳት በሰብዕና ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል ክስ መሰረተባቸው።

ከዚያ ኬንያታና ሩቶ ህብረት ፈጠሩና በ2013ቱ ምርጫ አሸነፉ። በምዕራባውያን የእጅ እዙር እሚፔሪያሊዝም የተከፈተብን ጥቃት ነው በማለት ኬንያውያን የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤትን ክስ እንዳይቀበሉ ሲሉ መቀስቀሱን ተያያዙት።

ኡሁሩ ኬንያታና ዊሊያም ሩቶ ዋናዋ የብጥብጥ አምባ በነበረችው በሪፍት ቫሊ ክፍለ ግዛት የገዢው ህብረታቸው ጸበኛ ማህበረሰቦችን እንዳስታረቀ ይናገራሉ ። ይሁን እንጂ ለበርካታ አሰርት ዓመታት በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል በመሬት ባለቤት በፖሌቲካና በብሔረሰባዊ ጉዳዮች የቀጠለው አምባጉዋሮ አላከተመም።

አንዳንዶች አሁን ያለው አስተዳደር ለሁለቱ መሪዎች ብሔረሰቦች ለኪኩዩና ካሊንጂዎች ያደላል ሲሉ ይከሳሉ መንግስቱ ያስተባብላል።

የፖለቲካ ተንታኝ ባራክ ሙሉካ፣ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ውሳኔ አጥፊ በተጠያቂነት አይያዝም የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብለዋል።

"ሰዎች በሀገር ውስጥም የሚነካኝ የለም ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤትም ምንም አያደርገኝም የሚል ዕምነት እንዲያድርባቸው ያደርጋል። ብጥብጥ እንደገና ሊቀሰቀስ ይችላል። ካካጌማ ውስጥ ብጥብጥ እንደነበር፣ ምክር ቤቱም ውስጥ ሰዉ ምን ዓይነት ባህሪ እያሳየ እንደሆነ ተመልክተናል ። ይህ ሁሉ የሚያሳየው ብጥብጡ እንደገና የመቀስቀሱ አደጋ ከፍተኛ መሆኑን ነው።" ብለዋል

በሌላ በኩል የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጊቱ ሙጋዪ መንግስታችን የፖሌቲካ ሁከት የሚያነሳሱ ሰዎች በተጠያቂነት የሚያዙበት መንገድ ያመቻቻል ብለዋል። ነቃፊዎች ግን ይሳካል የሚል ዕምነት የላቸውም።

የመብት ተሟጋቾች እንደሚያስገነዝቡት ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ኡሁሩ ኬንያታና ዊሊያም ሩቶ የተመሰረቱባቸውን ክሶች እንዲሰርዝ ያደረገው በሀገር ውስጥ የፍትህ ሂደቱ የፖለቲካ ሓይሎች ጣልቃ እየገቡ በማደናቀፋቸውና በምስክሮች ላይ ይደርስ በነበረው የማስፈራራት ተግባር ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ።

ከናይሮቢ መሃመድ ዩሱፍ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጂት ታዬ አቅርባዋለች፣ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል በመጫን ዝርዝሩን ያድምጡ።

የአይ ሲ ሲ ውሳኔ የቀጣዩን የኬኒያ ምርጫ አቅጣጫ ያመለክታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:55 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG