በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን መንግስት የብሄራዊ ስለላ እና ጸጥታ አገልግሎት የጋዜጠኞች ስብሰባ እንዳይካሄድ ከለከለ ተብሎ ተወንጅሏል


የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትር አህመድ ቢላል ለጋዜጠኞች ቃለ-ምልልስ እየሰጡ /ፋይል ፎቶ/
የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትር አህመድ ቢላል ለጋዜጠኞች ቃለ-ምልልስ እየሰጡ /ፋይል ፎቶ/

የሱዳን መንግስት የሃገሪቱ ዕለታዊ ጋዜጦች በተወሰኑ የፕሬስ ተቋማት ስር እንዲዋሃዱ በታለመው ዕቅዱ ዙሪያ ለመነጋገር የተጠራ የጋዜጠኞች ስብሰባ እንዳይካሄድ ከለከለ ተብሎ የቀረበውን ውንጀላ አስተባበለ።

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ መንግስቱ ባወጣው ዕቅድ ዙሪያ ለመናጋገር የተዘጋጀውን ሲምፖዚየም የመንግስቱ የብሄራዊ ስለላ እና ጸጥታ አገልግሎት እንዳይካሄድ አድርጓል ተብሎ ተወንጅሏል። የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አህመድ ቢላል እንደሚሉት ባሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ጋዜጦች ያላቸው ስርጭት አነስተኛ በመሆኑ አንድ ላይ ተዋህደው ቢንቀሳቀሱ መንግስት ለሚያደርግላቸው ድጋፍ ዋስትና ያገኙበታል በሚል በግድ ሳይሆን በውዴታ አብረው እንዲሰሩ ነው ይላሉ።

"መንግስት እኮ ሃሳብ አቀረበላቸው እንጂ እንዲዋሃዱ የሚያስግድድ ህግ የለም። ባሁኑ ጊዜ ያሉን ጋዜጦች ስርጭት በጣም አናሳ ነው። ግፋ ቢል ሶስት ወይ አራት ሺህ ቢሆን ነው፡ ሰላሳ ፍሬ የሚሸጡም አሉ ። ስለዚህ አንድ ላይ ሰፋ ያለ ስርጭት ቢያገኙ ይጠቅማቸዋል። መንግስትም ብድር በመስጠት ሊረዳቸው ይችላል።" ብለዋል።

የቅዳሜውን ውይይት ያዘጋጁ የጋዜጠኞች ማህበራት እንደሚሉት ግን የሱዳን መንግስት የተባለውን መመሪያ የሰጠው በቅርቡ በሀገሪቱ ስለተገደሉ ሁለት ተማሪዎች ጉዳይ ጋዜጠኞች እንዳይዘግቡ የብሄራዊ ስለላና ጸጥታ አገልግሎቶች መመሪያ መስጠትቱን ተከትሎ ነው።

በቅዳሜ ዕለቱ ሲምፖዚየም ከተለያዩ ጋዜጦች አሳታሚዎች፣ ዋና አዘጋጆች እና ጋዜጠኞች የመንግስቱ ዕቅድ በጋዜጦቻቸው ላይ ስለሚያስከትሉት አንደምታዎች ገለጻ እንዲያደርጉ ተጋብዘው ነበር።

ጋዜጦች ሲዋሃዱ በርካታ ባልደረቦቻችን ከስራ የመቀነስ አደጋ ላይ ይወድቃሉ የሚል ስጋት ያሰሙ ብዙዎች ናቸው።

የአሜሪካ ድምጹ ዘጋቢ ጄምስ በቲ ያጠናቀረውን አጭር ዘገባ ቆንጂት ታዬ ታቀርባለች።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG