ዋሽንግተን ዲሲ —
ከምንጊዜውም የገዘፈ በሆነው የጦርነት ስደተኞች ብዛት ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሄ ለመፈለግ የዓለም ሃገሮች ጥረታቸውን በዕጥፍ እንዲያሳድጉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ተማጽኖ አሰሙ።
ስዊዘርላንዱዋ ዳቮስ ከተማ እየተካሄደ ባለው የዓለም የኢኮኖሚ ጉባዔ ላይ ሚስተር ኬሪ ባደረጉት ንግግር የሌሎቹንም ዓለም አቀፍ ቀውሶች ሰለባዎች እንዲረዱና እየተባባሰ የመጣውን ሽብርተኝነት ከስረ መሰረቱ እንዲዋጉ ለዓለም መንግሥታቱ ተማጽኖ አቅርበዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በዚህ የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም. በኒው ዮርክ የዓለም የስደተኞች ቀውስን የተመለከተ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ እንደሚያስተናግዱ ሚስተር ኬሪ በዓለም የኢኮኖሚ ጉባዔ ላይ ይፋ አድርገዋል።
በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥም ንግግር አሰምተው ነበር ከዚህ በታች ካለው ቪድዮ ይመልከቱ።