ዋሽንግተን ዲሲ —
በርካታ የሚሳይል ተኩስ ሙከራዎችን በተከታታይ ስታካሂድ የቆየችው ሰሜን ኮሪያ ዛሬም ተወንጫፊ ሚሳይል በምስራቁ የባህር ጠረፍዋ ተወንጫፊ ሚሳይል ተኩሳለች ሲል የደቡብ ኮሪያ የዜና አገልግሎት ተናገረ።
ድርጊቱ ፒዮንግያንግ ከደቡብ ኮሪያና ከአጋሮቹዋ ጋር ያላትን ውጥረት የሚያባባስ መሆኑ ተመልክቷል።
ከየብስ ወደ ወደአየር ተወንጫፊው ሚሳይል ወደ ባህሩ የተተኮሰው ዛሬ ዓርብ ዕኩለ ቀን ላይ መሆኑን የደቡብ ኮሪያ ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት አውስታውቋል።