በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ወሲባዊ ጥቃት ፈጽመዋል ተብሎ በቀረበው ውንጀላ ላይ ብርቱ ምርመራ እንደሚካሄድ ቃል ገቡ


ፋይል ፎቶ - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዘይድ ራድ አል ሑሴን(Zeid Ra’ad al-Hussein)እ.አ.አ. 2016
ፋይል ፎቶ - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ዘይድ ራድ አል ሑሴን(Zeid Ra’ad al-Hussein)እ.አ.አ. 2016

ከቀረቡት ዘግናኝ ውንጀላዎች መካከል ቢያንስ ሶስት ልጃገረዶች የፍረንሳይ ወታደሮች በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ይዘውን ከውሻ ጋር ወሲብ ግንኙነት እንድንፈጽም አድርገውናል ሲሉ ለአንድ የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብት ባለስልጣን ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የፈረንሳይ መካከለኛ አፍሪካ ሪፑብሊክ ውስጥ ብዛት ባላቸው ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽመዋል ተብሎ በቀረበው ውንጀላ ላይ ብርቱ ምርመራ እንደሚካሄድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ቃል ገቡ።

ከቀረቡት ዘግናኝ ውንጀላዎች መካከል ቢያንስ ሶስት ልጃገረዶች የፍረንሳይ ወታደሮች በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ይዘውን ከውሻ ጋር ወሲብ ግንኙነት እንድንፈጽም አድርገውናል ሲሉ ለአንድ የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ መብት ባለስልጣን ተናግረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሳማንታ ፓወር አንዳንዶቹን የድርጊቱን ሰለባዎች ቤተሰቦች ጎብኝተዋል።

ወታደሮቹ ክህዝቡ አካባቢ እንዲወገዱ ቢደረግም የየሀገሮቻቸው መንግሥታት የበለጠ ርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል። "እየተወሰደ ያለው የመከላከል ርምጃ ጥሩ ነው። ግን እስካሁን ተጠያቂነት ስላልነበረ በዚሁ ይቀጥላል ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ፣ እዚህ ያለው አመመራር ያን ሊያስተካክል እየሞከረ ነው። ግን ወታደር የሚልኩት ሀገሮችም ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል።" ብለዋል።

የተባባሩት መንግስታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን የቀረቡት ውንጀላዎች እጅጉን እንደዘገነኗቸው ገልጸዋል። ፈረንሳይ በበኩልዋ ወታደሮችዋ ወንጀሉን መፈጸማቸው ከተረጋገጠ ከባድ ርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG