በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ምስራቃዊ ጠረፍ ክፍላተ ሀገር ብዙ ሚሊዮን ነዋሪዎች ወደ ወትሮአዊ ኑሮው ለመመልስ ቀናት መውሰዱ አይቀሬ ይመስላል

በዩናይትድ ስቴትስ ምስራቃዊ ጠረፍ ክፍላተ ሀገር ብዙ ሚሊዮን ነዋሪዎች ወደ ወትሮአዊ ኑሮው ለመመልስ ቀናት መውሰዱ አይቀሬ ይመስላል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:54 0:00

በዩናይትድ ስቴትስ ምስራቃዊ ጠረፍ ክፍላተ ሀገር ብዙ ሚሊዮን ነዋሪዎች ወደ ወትሮአዊ ኑሮው ለመመልስ ቀናት መውሰዱ አይቀሬ ይመስላል

ከክረምት በረዶ ሁኔታ በተያያዘ ምክንያት ቢያንስ ሃያ አራት ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

በረዶ በቀላቀለ ከባድ የክረምት ማዕበል፣ ጎርፍና ካሁን ቀደም ባልታየ መጠን የገዘፈ በረዶ የወረደባቸው በዩናይትድ ስቴትስ ምስራቃዊ ጠረፍ ክፍላተ ሀገር ብዙ ሚሊዮን ነዋሪዎች ወደወትሮአዊ ኑሮው ለመመልስ ቀናት መውሰዱ አይቀሬ ይመስላል።

ጎዳናዎቹዋን እና ህንጻዎችዋን ዙሪያ የሸፈነውን የበረዶ ናዳ ጠራርጋ ብቅ እያለች ባለችው በመዲናዋ በዋሽንግተን ዛሬ ሰኞ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ከአጣዳፊ ስራ ሰራተኞች በስተቀር ዝግ ሆነው ውለዋል። ለሁለት ቀናት ተቋርጦ የነበረው የምድር ውስጥ ባቡር ሜትሮ አገልግሎት በከፊል ጀምሯል።

የዋሽንግተንና የአካባቢዋ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው የዋሉ ሲሆን በዋና ዋናዎቹ የአካባቢው የአውሮፕላን ጣቢያዎች በጣም የተወሰኑ በረራዎች በከፊል ጀምረዋል።

ከክረምት በረዶ ሁኔታ በተያያዘ ምክንያት ቢያንስ ሃያ አራት ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። ከሞቱት ሰዎች መካከል የተከመረውን በረዶ በአካፋ ዝቀው ከደጃቸው በማስወገድ ላይ እንዳሉ በልብ ድካም ለህልፈት የተዳረጉም አሉባቸው።

XS
SM
MD
LG