ከስድሣ ሚሊየን ብር በላይ የፈሰሰበት የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ፋብሪካ ሰሞኑን አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የደቡብ ሱዳን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሃገሪቱን የመጀመሪያውን ገንዘብ በሞባይል የማስተላለፊያ አሠራር ይፋ አደረጉ።
የተያያዘው ቃለ-ምልልስ የኢትዮጵያን የዛሬ ጤና ይፈትሻል።
የነፃነት አዋጅ ከተነገረበት ከሰኔ 29/1768 ዓ.ም. እስከ ዛሬ ልክ 243 ዓመት ሆነ። ይህ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃ መንግሥት ዕድሜ ነው።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።
ለሱዳን የወቅቱ ሁኔታ እየተፈለገ ላለው መላ የዩናይትድ ስቴትስን አጋዥ ተሣትፎ ለማሳየት ያስችላል የተባለ ጉብኝት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትሯ ቲቦር ናዥ እያደረጉ ናቸው።
በኤርትራ መንግሥት ላይ የሚካሄደው ዓለምአቀፍ ክትትልና ፍተሻ እንዳይቆም ሰላሣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠይቀዋል።
ኮሌራ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት የሚያስከትል፤ ሰውነትንም ፈጥኖ ለድርቀት የሚያጋልጥ በረቂቅ ሕዋሳት ወይም ባክቴርያ የሚተላለፍ በሽታ ነው።
በአሜሪካ ድምፅ ከሰላሣ አንድ ዓመታት በላይ ያገለገለው ሰሎሞን ክፍሌ ከግንቦት 23/2011 ዓ.ም ጀምሮ ከመሥሪያ ቤቱ በጡረታ ተሰናብቷል።
የኢትዮጵያን ምጣኔ ኃብት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እገዛ ያደርጋል ተብሎ የታመነበትን የአሜሪካን መዋዕለ ነዋይ ፍሰት ለማፋጠን የታሰበ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ የኢትዮጵያ አጋርነት ጉባዔ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እየተካሄደ ነው።
ዛሬ ልክ የዛሬ 78 ዓመት የፋሽስት ጣልያን ወራሪ ኃይል ድል ተነስቶ ከተባረረ በኋላ ዋና ከተማዪቱን በያዘ ልክ በአምስት ዓመቱ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አዲስ አበባ ተመልሰው ገቡ።
በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው ግንኙነት ሥራ ፈጠራን በመደገፍና በዘላቂ መዋዕለ-ነዋይ ላይ ያዘነበለ እንዲሆን ለማስቻል እንደሚሠሩ አዲሱ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል። የሹመት ደብዳቤአቸውን ሰሞኑን ለፕሬዚዳንት ትረምፕ ያቀረቡት አምባሳደር ፍፁም ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ለውጡ በውጤታማና በተረጋጋ መንገድ እንዲቀጥል ለማድረግ እንዲተጉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ቃለ-ምልልሱን ከተያያዘው ቪድዮ ያገኛሉ።
የደቡብ ሱዳንን ለአምስት ዓመታት የዘለቀ የርስ በርስ ብጥብጥ ለማስቆም ያስችላል የተባለውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ጥቂት ሳምንታት ሲቀሩት የሃገሪቱ የሃይማኖትና ሲቪክ መሪዎች የሚሣተፉበት የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ሊካሄድ ታቅዷል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲውን የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ብሩክ ኃይሉን የክብር ቆንሲል አድርጎ ሾሟል።
ኤርትራ ውስጥ ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ደብዛቸው የጠፋ ሰዎች ምን እንደሆኑ ወይም የሚገኙበትን ሁኔታ መንግሥቷ እንዲያሳውቅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ጠየቁ።
የእንግሊዝን ከአውሮፓ ኅብረት የመውጣት ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትሯ እጅ ለማውጣትና እራሳቸው ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ድምፅ የሃገሪቱ እንደራሴዎች ትናንት ምሽት ላይ ሰጥተዋል።
በጁፒተር አካባቢ ያሉ ግዙፍ አለቶችን ወይም አስቴሮይዶችን ተፈጥሮና ይዘት ለመመርመር የታቀዱ የአሜሪካው ብሄራዊ የኤሮኖቲክስና የጠፈር አስተዳደር - ናሳ ተልዕኮዎች ከሆኑት አንደኛዋ መንኩራኩር በኢትዮጵያዪቱ “ድንቅነሽ” ስም ተሰይማለች።
ኅብረተሰቡ “ከሃሰት ዜናና ከጥላቻ ንግግሮች እንዲቆጠብ” ሲል የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት አሳስቧል።
ካፕተን አንተሁነኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባልደረባ ሆነው ለሰላሣ ዘጠኝ ዓመታት በተለያዩ ደረጃዎች አገልግለዋል።
የቀድሞ የበረራ አስተናጋጅ፤ የአየር መንገዱ የሞተር ፑል የቀድሞ ፎርማን፤ የቴክኒክ ክፍሉና የማሰልጠኛው ባለሙያ የነበሩ ስለአየር መንገዱ ያላቸውን ዕውቀትና ሃሣባቸውን ለቪኦኤ አካፍለዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ