በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኤርትራ ላይ የቀረቡ ስሞታዎችና ለመሪዋ የተፃፈ ደብዳቤ


በኤርትራ መንግሥት ላይ የሚካሄደው ዓለምአቀፍ ክትትልና ፍተሻ እንዳይቆም ሰላሣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠይቀዋል።

በኤርትራ መንግሥት ላይ የሚካሄደው ዓለምአቀፍ ክትትልና ፍተሻ እንዳይቆም ሰላሣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠይቀዋል።

ድርጅቶቹ ጥያቄያቸውን ማክሰኞ፣ ሰኔ 4 / 2011 ዓ.ም. ያቀረቡት ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ 41ኛ ስብሰባ ባስገቡት ፊርማቸውን በጋራ ባኖሩበት ደብዳቤ ነው።

የድርጅቶቹ አቤቱታ ኤርትራ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አሁንም እስከፊ እንደሆነ መሆኑን ይናገራል።

“በቅርቡ በአካባቢው የተካሄዱ ለውጦች ... እንኳ ኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታዋን እንድታሻሻል አላገዙም” ይላል ደብዳቤው።

ኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ አባል እንድትሆን መመረጧ ግዴዎቿን እንድትወጣና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተላለፉባትን ውሣኔዎች እንድታከብር የሚያደርጓት መሆናቸውን ድርጅቶቹ አስታውሰው “ሃገሪቱ እያካሄደች ነው” የሚባሉ “ጥሰቶችን በቸልታ ማለፍ ጥፋትን እንደመሸለም ይቆጠራል” ሲሉ አሳስበዋል።

“በመሆኑም - ይላል የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾቹ ድርጅቶችና ቡድኖች ጥያቄ - የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ በመጭው 41ኛ ጉባዔው ወቅት በኤርትራ ላይ የሚካሄደው ክትትልና ፍተሻ እንዳይቋረጥ የሚያደርግ ውሣኔ እንዲተላለፍ፤” አክለውም ‘ተፈፅመዋል ወይም እየተፈፀሙ ናቸው’ ላሏቸው ጥሰቶችም ኃላፊዎቹ የሚጠየቁበት ሁኔታ እንዲፈጠር ጠይቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሰኞ፣ ሰኔ 3/2011 ዓ.ም. ለፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ግልፅ ደብዳቤ የፃፉ 102 በዓለምአቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ አፍሪካዊያን በሃገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ እያሳሰባቸው መሆኑን ገልፀው “የጋራ” ያሏቸውን ችግሮች በጋራ ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልፀውላቸዋል።

የኤርትራ መንግሥት በሻባይት ዌብሳይቱ ላይ ባወጣው አጭር ርዕሰ-አንቀፅ ታዋቂዎቹ አፍሪካዊያን ለፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ የላኩትን ግልፅ ደብዳቤ አስመልክቶ “ሰማዕቶቻችንና ለስድሣ ዓመታት ዓለምአቀፉ ኅብረተሰብና ተላላኪዎቻቸው ያደረሱብንን ግፍ በጥሞና በምናስብበት ሰኔ ወር ቡድኑ ደብዳቤውን መላኩና ማሠራጨቱ በቡድኑ ዓላማ ላይ ጥያቄ ያስነሣል” ብሏል።

“ኤርትራ ከዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አልተገለለችም” ይልና የሻባይት ርዕሰ አንቀፅ “የደብዳቤው ላኪዎች ላለፉት ሃያ ዓመታት በኤርትራ ላይ ሲነዛ የኖረው አሉታዊ ፕሮፓጋንዳ ሰለባዎች ናቸው፤ አንዳቸውም ስለ ኤርትራ ፈተናዎች በጎ ነገር ፅፈው አያውቁም፤ እንዲያውም አንዳንዶቹ በሃያላን ሃገሮች ጋር ትሥሥር ያላቸው ናቸው ብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኤርትራ ላይ የቀረቡ ስሞታዎችና ለመሪዋ የተፃፈ ደብዳቤ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:14 0:00

የዌብ ማገናኛዎቹን እየተከተሉ ሙሉ ደብዳቤዎችንና ምላሹን ያንብቡ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG