በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናዥ ባዲሳባና በኻርቱም

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ /ግራ/፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው /ቀኝ/ - አዲስ አበባ፣ ዓርብ ሰኔ 7/2011 ዓ.ም
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥ /ግራ/፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው /ቀኝ/ - አዲስ አበባ፣ ዓርብ ሰኔ 7/2011 ዓ.ም

ለሱዳን የወቅቱ ሁኔታ እየተፈለገ ላለው መላ የዩናይትድ ስቴትስን አጋዥ ተሣትፎ ለማሳየት ያስችላል የተባለ ጉብኝት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትሯ ቲቦር ናዥ እያደረጉ ናቸው።

ለሱዳን የወቅቱ ሁኔታ እየተፈለገ ላለው መላ የዩናይትድ ስቴትስን አጋዥ ተሣትፎ ለማሳየት ያስችላል የተባለ ጉብኝት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትሯ ቲቦር ናዥ እያደረጉ ናቸው።

አምባሳደር ናዥ ዛሬ፣ ዓርብ ከዋሉባት ከአዲስ አበባ ከቪኦኤ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ዩናይትድ ስቴትስ በሁለቱም የሱዳን ወገኖች ዘንድ አዎንታዊ መጠናከርን ለመፍጠር እየሠራች መሆኗን አመልክተዋል።

ወታደራዊው ምክር ቤት ብቻውን አካሂደዋለሁ የሚለው ምርጫ “በማንም” ተዓማኒነት እንደማይኖረው፤ የለውጥና የነፃነት ኃይሎቹ በተናጠል አዲስ መንግሥት ለመመሥረት ቢያስቡም ውጤቱ ጉዳት እንደሚሆን አምባሳደር ናዥ አሳስበዋል።

ሃገራቸው ከጅምሩ አንስቶ እገዛ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኗን ያመለከቱት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናዥ ዩናይትድ ስቴትስ በጉዳዩ ውስጥ መግባት ከሚፈልጉ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ ካሉ ሁሉም ወገኖች ጋር መሥራቷን እና ማስተባበሯን እንደምትቀጥል አመልክተው ጉዳዩን በቅርብ እንዲከተታተሉ የሃገራቸው ልዩ ልዑክ እንዲሆኑ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ መመደባቸውን አስታውቀዋል።

የሱዳን ጉዳይ ለአካባቢው እጅግ አስጊ እንደሚሆንና የሱዳን ጎረቤቶችም መግባባትና ሰላም እንዲሰፍን ንቁ ተሣትፎ እንደሚጠበቅባቸው ሲናገሩ “ግብፅ በደቡብ ድንበሯ ማየት የምትፈልገው የመጨረሻ ነገር ሌላ ሊብያን ነው፤ ኢትዮጵያም በሰሜን ምዕራብ ድንበሯ ማየት የምትፈልገው የመጨረሻ ነገር ሌላ ሶማልያን ነው” ብለዋል።

አምባሳደር ናዥ ከኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን አምባሳደሩ ኻርቱም ላይ ስለነበራቸው ቆይታና የታዘቡትንም ለሚኒስትሩ አጫውተዋቸዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ናዥ ባዲሳባና በኻርቱም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG