በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለኤርትራ የመብቶች አያያዝ


ኤርትራ ውስጥ ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ደብዛቸው የጠፋ ሰዎች ምን እንደሆኑ ወይም የሚገኙበትን ሁኔታ መንግሥቷ እንዲያሳውቅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ጠየቁ።

ኤርትራ ሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለምአቀፍ ስምምነትን አተገባበር የሚከታተለው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ እያጠናቸው ካሉ ሰባት ሃገሮች አንዷ ነች።

የኤርትራን የዛሬ ሁኔታ እየቃኙ ያሉት 18 ነፃ ናቸው የሚባሉ ባለሙያዎች እያሳሰበቧቸው ያሉ ብዙ ጉዳዮች እንዳሉ እየተነጋገሩ ናቸው።

ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች፣ ማሰቃየት፣ የሰዎችን ደብዛ ማጥፋት እና ሌሎችም የበረቱ የሚባሉ ረገጣዎችን የያዙ ክሦች እየደረሱት መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል።

ከባለሙያዎቹ አንዱ የሆኑት የደቡብ አፍሪካው ክሪስቶፍ ሄይነስ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል የኮሚቴው አባላት ከኤርትራ ልዑካን ጋር ፍሬያማ ውይይቶችን ለማድረግ በሚል ተስፋ በርካታ ጭብጦችን አንስተው እንደነበረ ተናግረዋል።

ከጭብጮቹ መካከል በ1993 ዓ.ም. ተይዘው የነበሩ 18 ጋዜጠኞች ጉዳይ እንደሚገኝበትና በሕይወት ይኑሩ አይኑሩ የሚያውቅ እንደሌለ ሄይነስ ገልፀዋል።

በዚያው ዓመት የታሠሩ የፍትህና የዴሞክራሲ ሕዝባዊ ግንባር የሚባል ፓርቲ ያቋቋሙ 11 የመንግሥቱ የቀድሞ ባለሥልጣናት ዕጣ ፈንታም እንዲሁ የሚያሳስባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ስለኤርትራ የመብቶች አያያዝ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:39 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG