በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሉሲ በሰማይ ላይ

በጁፒተር አካባቢ ያሉ ግዙፍ አለቶችን ወይም አስቴሮይዶችን ተፈጥሮና ይዘት ለመመርመር የታቀዱ የአሜሪካው ብሄራዊ የኤሮኖቲክስና የጠፈር አስተዳደር - ናሳ ተልዕኮዎች ከሆኑት አንደኛዋ መንኩራኩር በኢትዮጵያዪቱ “ድንቅነሽ” ስም ተሰይማለች።

በጁፒተር አካባቢ ያሉ ግዙፍ አለቶችን ወይም አስቴሮይዶችን ተፈጥሮና ይዘት ለመመርመር የታቀዱ የአሜሪካው ብሄራዊ የኤሮኖቲክስና የጠፈር አስተዳደር - ናሳ ተልዕኮዎች ከሆኑት አንደኛዋ መንኩራኩር በኢትዮጵያዪቱ “ድንቅነሽ” ስም ተሰይማለች።

“ሉሲ” ተብላ የምትጠራው መንኩራኩር ወደ ጁፒተር ምኅዋር የምትተኮሰው ከሁለት ዓመታት በኋላ መሆኑንና ከአራት ዓመታት የጠፈር ላይ ጉዞ በኋላ ከምትቃኛቸው አለቶች የመጀመሪያው ጋ እንደምትደርስ የናሳ ሳይንቲስቱና የጎዳርድ የበረራ ማዕከል አሶሺየት ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ላቀው ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የ “ሉሲ” ቡድን አባላት ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ በየክልሉ እየተዘዋወረች ላለችው “ሉሲ” ተልዕኮዋ የተሣካ እንዲሆን መልዕክታቸውን በትዊተር አስተላልፈውላታል።

የቡድኑ መሪም የፊታችን መስከረም ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ንግግር እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እየጣሩ መሆናቸውን ዶ/ር ብሩክ ላቀው ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሉሲ በሰማይ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:19 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG