በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ - አሜሪካ አጋርነት መድረክ

አምባሳደር ማይክ ሬይነር እና አምባሳደር ቲቦር ናዥ /ከግራ ወደ ቀኝ/ የኢትዮጵያ የአጋርነት መድረክ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት - 07-09-11 ዓ.ም
አምባሳደር ማይክ ሬይነር እና አምባሳደር ቲቦር ናዥ /ከግራ ወደ ቀኝ/ የኢትዮጵያ የአጋርነት መድረክ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት - 07-09-11 ዓ.ም

የኢትዮጵያን ምጣኔ ኃብት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እገዛ ያደርጋል ተብሎ የታመነበትን የአሜሪካን መዋዕለ ነዋይ ፍሰት ለማፋጠን የታሰበ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ የኢትዮጵያ አጋርነት ጉባዔ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እየተካሄደ ነው።

አምባሳደር ፍፁም አረጋ - የኢትዮጵያ የአጋርነት መድረክ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት - 07-09-11 ዓ.ም.
አምባሳደር ፍፁም አረጋ - የኢትዮጵያ የአጋርነት መድረክ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት - 07-09-11 ዓ.ም.

​ኢትዮጵያ በቅርቡ የጀመረችውንና አሁንም እየሠራችበት ያለችበትን የምጣኔ ኃብት ማሻሻያዎች እርምጃና እየተሟሟቁ ያሉትን የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች ለማስተዋወቅ የታሰበ መድረክ መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ደረጃ ሲዘጋጅ በዓይነቱ እጅግ አልፎ አልፎ በሚታየው ከዓለም ሃገሮች አንድ ሃገር ላይ አተኩሮ በሚካሄድ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት አማካሪ ሚኒስትር ዶ/ር አርከበ እቁባይ እና በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ሃገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ባሉ ለውጦችና ለግል መዋዕለ-ነዋይ እየተከፈቱ ባሉ መስኮች ላይ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል።

ዶ/ር አርከበ እቁባይ - የኢትዮጵያ አጋርነት መድረክ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት - 07-09-11 ዓ.ም.
ዶ/ር አርከበ እቁባይ - የኢትዮጵያ አጋርነት መድረክ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት - 07-09-11 ዓ.ም.

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የምጣኔ ኃብት መናኸሪያ ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ በግብርና፣ በመሠረተ-ልማት፣ በኢነርጂ፣ በአምራች ኢንዱስትሪዎችና በአገልግሎት ዘርፎች መስኮቹ መከፈታቸውን፣ የአሠሪና ሠራተኛ ሕግም እየተሻሻለ መሆኑን ኢትዮጵያዊያኑ ባለሥልጣናት አመልክተው ለመዋዕለ-ነዋይ አፍሳሾች የቀለለ ሁኔታ ለመፍጠር የኢንቨስትመንት ኮሚሽኑ የከፈተውን ማጉላላትና ምልልስን የሚያስወግድ አሠራርም አስተዋውቀዋል።

የኢትዮጵያ የአጋርነት መድረክ - ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት
የኢትዮጵያ የአጋርነት መድረክ - ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት

ኢትዮጵያ የገባችበትን የለውጥ መንገድ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ አድንቀው የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናዥና በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነርም ኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብቷን ለማሳደግና ለመሸጋገር የያዘችው እንቅስቃሴ የተሣካ እንዲሆን ሃገራቸው ማንኛውንም እገዛ እንደምታደርግ እነርሱም በየግላቸው የሚቻላቸውን ሁሉ ከማድረግ እንደማይቦዝኑ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ - አሜሪካ አጋርነት መድረክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:36 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG