ባለፈው ዕሁድ ቢሾፍቱ አቅራቢያ በወደቀው የአይሮፕላን አደጋ ስለሞቱት ዜጎች ዛሬ (ዕሁድ) ኢትዮጵያ ውስጥ በተከናወነ ሥነ-ሥርዓት ላይ የወጣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሰው የሃገሪቱን ብሄራዊ ባንዲራ የለበሱ 17 ባዶ የአስከሬን ሣጥኖችን አጅቧል።
በዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የሚኖሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ሠራተኞች የቀድሞ ባልደረቦቻቸውን ለመዘከርና በቢሾፍቱው አደጋ ሕይወታቸው ለጠፋ ተሣፋሪዎች የፀሎትና የመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓት አዘጋጅተዋል።
ቦይንግ አሁን ሥራ ላይ ያለውን የአሠራር መመሪያ እንደማይለውጥ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት ከሆነውና ትናንት ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን ስብርባሪ ውስጥ የተገኘው የመረጃ መዝጋቢ ሳጥን ርክክብ መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለቪኦኤ ገልፀዋል።
በእንደራሴ ኬረን ባስ እየተመራ በኢትዮጵያና በኤርትራ ጉብኝት ያደረገው የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የልዑካን ቡድን ሥራውን አጠናቅቆ ዛሬ ዋሺንግተን ዲሲ ገብቷል።
ከአንድ ወር ተኩል በላይ ይፈጅ የነበረው አገልግሎት ወደ ሁለት ቀናት ወርዷል፤ ክፍያውም ዝቅ ብሏል፤ የወካይና ተወካይን ዋሺንግተን ላይ በአካል መገኘትና መገናኘት አይጠይቅም።
በሜሪላንድ መንግሥት የተመዘገበ ኢትዮ-አሜሪካን የንግድ ምክር ቤት በሲልቨር ስፕሪንጉ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ በጠራው የፊታችን ዕሁድ ከቀትር በኋላ በሚያካሂደው ጉባዔ ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዛሬ፤ ማክሰኞ - ጥር 28/2019 ዓ.ም. ምሽት ላይ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ በሃገራቸው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ንግግር ያደርጋሉ። በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በተወካዮች ምክር ቤቱ አፈጉባዔ ናንሲ ፔለሲ መካከል የተፈጠረው መፋጠጥ ለውጥ አላሳየም። ሌላ የመንግሥት መዘጋት ዙር፣ ወይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥጋት አሜሪካ ላይ አንዣብቧል።
“... አብይ አሕመድ ጥረቶቻቸው እንደሚሳኩላቸው የብዙዎች ተስፋ ነው ...” ሲል ፎረን ፖሊሲ ፅፏል።
ራዕይ ለኢትዮጵያ ወይም ቪዥን ኢትዮጵያ የሚባለው የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ምሁራን ስብስብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲያካሂድ የመጀመሪያ የሆነውን ስብሰባውን ባለፈው ወር አዲስ አበባ ላይ አካሂዷል።
ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ሆቴል ላይ ሰሞኑን አል-ሸባብ ያደረሰውን ጥቃት የተቃወሙ ሶማሊያዊያን ዛሬ ኢስትሌ ቀበሌ ውስጥ ሰልፍ ወጥተዋል።
የሱዳን መንግሥት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እያካሄደ ነው ያለውን ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ እንዲያቆም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ከሚሽነር ሚሼል ባሸሌ ጠየቁ።
የኬንያ መንግሥትና ተቃዋሚዎቹ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ትናንት አደጋ በጣሉ ሽብርተኞች ላይ እጅግ ብርቱ የተባለ ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሯቸው እንቅስቃሴዎች፤ በዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ፣ እንዲሁም በአትላንታ-ጆርጂያ በተለያዩ የሙያ፣ የንግድ፣ የበጎ አድራጎት፣ የድጋፍና ሌሎችም ተግባሮቻቸው የሚታወቁት የአቶ ሰሎሞን በቀለ አስከሬን ዛሬ ተሸኝቷል።
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በወዲያኛው ሣምንት ማብቂያ ባደረገው 15ኛ መደበኛ ጉባዔው ማብቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ የብሄራዊ አንድነት መንግሥት እንዲመሠረትና የምርጫ ቦርድ ተዓማኒ ሊሆን በሚችል ሁኔታ እንዲዋቀር ጠይቋል።
የኢሕአዴግ እንደራሴዎች እራሣቸው 'መቶ ከመቶ ሊባል በሚችል ድጋፍ ተመርጠናል' ብለው ዛሬም ያምናሉ? ለመሆኑ ፓርላማው ቀልቡ ምን ይነግረዋል? እምነቱስ ምንድነው? በእውኑ ሕዝባዊ ፓርላማ ነኝ ይላል? እራሱንስ ገምግሞ ያውቃል?
ሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ በማልታ ደሴት አቅራቢያ በሁለት የጀርመን ጀልባዎች ላይ ማረፊያ አጥተው የቆዩ አርባ ዘጠኝ ፍልሰተኞችን እንደሚያስተናግዱ የደሴቲቱ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ጆዜፍ ማስካት ዛሬ አስታወቁ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር ሃገሪቱ ከሜክሲኮ ጋር የምትዋሰንበት የደቡብ ድንበር አካባቢ ያለው ሁኔታ የማይቀር “የሰብዓዊና የብሄራዊ ፀጥታ ቀውስ” ነው የሚል ዕምነት ለማሥረፅ በብርቱ እየገፋ መሆኑ ተገልጿል።
ዓለም አዲሱን የአውሮፓ 2019 ዓ.ም. ስታስተናግድ ዋናና ትላልቅ ከተሞች ደምቀው አንግተዋል።
“ቪዥን ኢትዮጵያ” ወይም “ራዕይ ለኢትዮጵያ” የሚባለው ሲቪክ የምሁራን ስብስብ ሰባተኛ ጉባዔውን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያካሂድ ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ