በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ባልደረቦች


ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ /ፎቶ ፋይል/
ቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ /ፎቶ ፋይል/

የቀድሞ የበረራ አስተናጋጅ፤ የአየር መንገዱ የሞተር ፑል የቀድሞ ፎርማን፤ የቴክኒክ ክፍሉና የማሰልጠኛው ባለሙያ የነበሩ ስለአየር መንገዱ ያላቸውን ዕውቀትና ሃሣባቸውን ለቪኦኤ አካፍለዋል።

በዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የሚኖሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ሠራተኞች የቀድሞ ባልደረቦቻቸውንና በቢሾፍቱው አደጋ ሕይወታቸው ለጠፋ ተሣፋሪዎች የፀሎትና የመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል።

በቨርጂንያው ኮሎምቢያ ፓይክ እና ሳውዝ ሃይላንድ መንገዶች ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ልማት ድርጅት ውስጥ የተሰናዳው ዝግጅት በዋሺንግተን ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከሁለት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት (አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ከምሽቱ አምስት ሰዓት እስኪሆን) የተከናወነ ነው።

ከአስተባባሪዎቹ መካከል የሆኑት የቀድሞ የበረራ አስተናጋጅ ወ/ሮ ክበበ ጌራወርቅ፤ የአየር መንገዱ የሞተር ፑል የቀድሞ ፎርማን አቶ ገነነ አበበ፤ የቴክኒክ ክፍሉና የማሰልጠኛው ባለሙያ የነበሩት አቶ ስመኝ ይፍሩ ስለአየር መንገዱ ያላቸውን ዕውቀትና ሃሣባቸውን ለቪኦኤ አካፍለዋል።

ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ባልደረቦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:05 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG