በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ንግድና ምጣኔ ኃብት


ከስድሣ ሚሊየን ብር በላይ የፈሰሰበት የጎሽ ሜዳ ቧንቧና ፕላስቲክ ፋብሪካ ሰሞኑን አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የፋብሪካው ግንባታ በተያዙለት ሁለት ደረጃዎች ሙሉ በሙሊ ሲጠናቀቅ አጠቃላዩ መዋዕለ-ነዋይ ከ230 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚሆን ተነግሯል።

ደሴን ከምዕራብ ወረዳዎች ጋር በሚያገናኘው ገራዶ ሜዳ ላይ የቆመው ይህ ፋብሪካ ለግብርናና ለግንባታ ሥራዎች ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን የሚያወጣ ሲሆን እስከአሁን በሃገር ውስጥ የማይሠሩ ውጤቶችንም ለገበያና ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

በሌላ የንግድና ምጣኔ ኃብት ዘገባ፤ የዩናይትድ ስቴትሱ የአፍሪካ የዕድገትና የተጠቃሚነት ዕድሎች ድንጋጌ /አጎአ/ ተጠቃሚ ሃገሮች የያዝነው የአውሮፓው 2019 ዓ.ም. የምክክር መድረክ በምዕራብ አፍሪካዪቱ አይቮሪ ኮስት የአትላንቲክ የንግድ መናኸሪያ ከተማ አቢዦን ላይ ተካሂዷል።

በዚህ ዕሁድ፤ ሐምሌ 28/2011 ዓ.ም. ተጀምሮ ማክሰኞ፣ ሐምሌ 30/2011 ዓ.ም. በተጠናቀቀው 18ኛው የአጎአ ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ የዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ከሰሃራ በስተደቡብ ያሉ ሃገሮች የንግድና የዲፕሉማሲ ባለሥልጠናትና እንዲሣተፉ የተጋበዙ፣ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የንግድና የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ይህ በልማት ወደኋላ የቀሩ የአፍሪካ ሃገሮችን ለመድገፍና ምርቶቻቸወን ያለቀረጥ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ገበያ ማስገበት እንዲችሉ ታስቦ የዛሬ 19 ዓመት የወጣ ሕግ ከዚህ ቀደም ለሁለት ጉዜ የተራዘመ ሲሆን የአሁኑ የተቃሚነት ጊዜ የሚያበቃው በመጭዎቹ ስድስት ዓመታት ውስጥ ነው።

በአፍሪካዊያንና በአሜሪካዊያን ባለሙያዎች፣ ባለሥልጣናትና ታዛቢዎች ዕምነት አፍሪካ ከግዙፉና ከካብታሙ የአሜሪካ ገበያ እንድትጠቀም የተሰጣትን ዕድል በአግባቡ ሳትጠቀምበት ቀርታለች።

ለተጨማሪ ዘገባዎቹ ያሉበትን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ንግድና ምጣኔ ኃብት
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:45 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG