ኢትዮጵያ ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ኅዳሴ ግድብን መሙላት እንዳትጀምር የሚያሳስበው የዩናይትድ ስቴትስ መግለጫ ተገቢ ያልሆነና የዛሬ ሦስት ዓመት ከተፈረመው የመርኆች ስምምነት ጋር የሚጋጭ እንደሆነ የኢትዮጵያ የውኃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ አስታውቀዋል።
በኅዳሴ ጉዳይ የዋሺንግተን ድርድር - ከአቶ ጌዲዮን አስፋው ጋር የተደረገ ቃለምልልስ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ የጀመሩት ድርድር ከሁለት ሣምንት ሳይቋጭ ነበር የተበተነው። በውኃው አሞላልና ጊዜ፣ በኋላም በሥራው አመራር ወይም ኦፐሬሽን ላይ ነው ውገኖቹ ሲደራደሩ የቆዩት። የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች በጊዜውና በመጠንም ሆነ፣ “’ታዛቢ’ ይሆናሉ” ከተባሉት ወገኖች ያልጣማቸው ነገር እንደነበረ ነው የሚሰማው።
የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሃገራቸው በ2020 ዓ.ም. የምትገኝበትን ሁኔታ በዝርዝር የሚያብራራ ንግግር /State of the Union Address/ ለ116ኛው የተወካዮች ምክር ቤት ጥምር ጉባዔ አድርገዋል።
የደኅንነት ደረጃዎችን አያሟሉም ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በፈረጇቸው ስድስት ተጨማሪ ሃገሮች ላይ የትረምፕ አስተዳደር በሕጋዊው ኢሚግሬሽን ላይ ገደብ እንደሚጥል አስታውቋል።
ግብጽ በአሁኑ አቋሟ የምትቀጥል ከሆነ የታላቁ ህዳሴን ግድብ አሞላል እና አጠቃቀምን በተመለከተ ስምምነት ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል በዮናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጠቆሙ።
ከቻይና ጋር በንግድና ሌሎችም የምጣኔ ኃብት መስኮች የተሳሰረቸ ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መዛመት ጉዳይ ከሚያሳስባቸው ሀገሮች አንዷ እንደሆነች እየተነገረ ነው።
ዛሬ የሲቪል መብቶች ተሟጋቹ የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት ቀን ነው። በዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ክብረ በዓል ነው።
ፕሬዚዳንት ትረምፕ ባለፈው ሣምንት ስለ ኖቤል የሰላም ሽልማት የተናገሩት "ኤርትራ ግብፅ መስላቸው ነው" የሚሉ አስተያየቶች እየተሰሙ ነው።
ኢራን የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በሚገኙባቸው የኢራቅ የጦር መደቦች ላይ የሚሳየል ጥቃት ካደረሰች በኋላ ዛሬ ረፋድ ላይ ከዋይት ሃውስ የተናገሩት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አንደበታቸው በአመዛኙ የተለሳለሰ ነበር።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ “ከመቼውም ጊዜ በላይ የተወሳሰበ ነው” ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አጠቃላይ የሃገራዊ ንግግር መድረክ እንዲጠራ ጠይቋል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፤
ከኢትዮጵያ፣ ከግብፅና ከሱዳን ከፍተኛ ተጠሪዎች ጋር ዛሬ መገናኘታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የሚያስከስስ እና ከሥልጣን የሚያስነሳ ጥፋት ፈፅመው እንደሆነ በተወካዮች ምክር ቤቱ የተጀመረውን ምርመራ ተቋማዊ ቅርፅ ለማስያዝ የታሰበ ድምፅ ትናንት በእንደራሴዎቹ ተሰጥቷል።
የትረምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያን፣ የግብፅንና የሱዳንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ጋብዟል።
“የአዳማ ፀጥታ ዛሬ የተሻለ ነው” - የከተማይቱ አስተዳደር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀመሩትን የመደመር እሣቤና “ለአካባቢው ሀገሮች አስፈላጊ ነው” ያሉትን የሰላምና የመተባበር መንገድ ሶቺ ላይ አጉልተው ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን ዩናይትድ ስቴትስ እንደምታደንቅ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ አስታወቀ። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ የወጣውና በመሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ቢሮ የተሰራጨው መልዕክት “እጅግ የተከበረው የኖቤል የሰላም ሽልማት መቶኛ ተቀባይ በመሆናቸው ዩናይትድ ስቴስት ለዶ/ር አብይ አሕመድ ደስታዋን ትለገልፃለች” ይላል።
የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ሐሣባቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አካፍለዋል፡፡
የኢትዮጵያዊነት ኢንስቲትዩት እና ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ ከሥነ-ዜጋ ትምህርትና ኢትዮጵያዊ ሥነ-ምግባር የታሪክን እውነተኛ ምንጮች እስከመፈተሽ፣ የሃሰት ትረካዎችን እስከማጋለጥና ማስተካከል፣ በኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባትና በሃገራዊ ፍቅርና ክብር መተሣሰርን እስከ ማፅናት የሚደርስ ሥራ እንደሚያከናውኑ የድርጅቱና የተቋሙ መሥራቾችና መሪዎች ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሰሞኑን በመደዳ የተኩስ ጥቃቶች 31 ሰው የተገደለባቸውን የማዕከላዊ ምዕራቧን ኦሃዮ ከተማ ዴይተንና የደቡቧን ቴክሳስ ግዛት ኤል-ፓሶን ዛሬ፣ ነኀሴ 1/2011 ዓ.ም. እየጎበኙ ናቸው።
ተጨማሪ ይጫኑ