በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብጽ በአሁኑ አቋሟ ከቀጠለች ስምምነት ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተጠቆመ


ታላቁ የህዳሴ ግድብ
ታላቁ የህዳሴ ግድብ

ግብጽ በአሁኑ አቋሟ የምትቀጥል ከሆነ የታላቁ ህዳሴን ግድብ አሞላል እና አጠቃቀምን በተመለከተ ስምምነት ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል በዮናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጠቆሙ።

አምባሳደር ፍጹም አረጋ ይሄን የገለጹት ለሶስት ቀናት የፈጀው እና ሶስቱ ሀገራት በሚኒስትር ደረጃ ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ማብቃቱን አስመልክቶ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው።

የሀገራቱ ድርድር የመጨረሻ የስምምነት ሰነድ እንዲዘጋጅ ለቴክኒክ እና ህግ ባለሙያዎች ትዕዛዝ መሰጠቱ ይፋ በሆነበት በአሁኑ ሰዓት አምባሳደሩ ግብጽ ፈጣን ስምምነት ላይ እንዲደረስ ፍላጎት እንዳላት ብታሳይም፣በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያላት አቋም ግን የሚፈለገውን ስምምነት እንዳያዘገየው እንደሚሰጉም ጠቁመዋል።

አምባሳደር ፍጹም አረጋ ከሀብታሙ ስዩም ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ እንስማ።

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጽ በአሁኑ አቋሟ ከቀጠለች ስምምነት ላይ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:10 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG