በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ


ዶ/ር እርቁ ይመር /በስተቀኝ/፣ አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሄር /በስተግራ/
ዶ/ር እርቁ ይመር /በስተቀኝ/፣ አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሄር /በስተግራ/

የኢትዮጵያዊነት ኢንስቲትዩት እና ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ ከሥነ-ዜጋ ትምህርትና ኢትዮጵያዊ ሥነ-ምግባር የታሪክን እውነተኛ ምንጮች እስከመፈተሽ፣ የሃሰት ትረካዎችን እስከማጋለጥና ማስተካከል፣ በኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባትና በሃገራዊ ፍቅርና ክብር መተሣሰርን እስከ ማፅናት የሚደርስ ሥራ እንደሚያከናውኑ የድርጅቱና የተቋሙ መሥራቾችና መሪዎች ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያዊነት - የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ
ኢትዮጵያዊነት - የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ

“የሃገሩን ታሪክና የአብሮነት እሴቶች የማያውቅ ሰው እንደ ሕፃን ይቆጠራል” ብሏል ያሉትን የጥንቱን የሮማ የመንግሥት ሰው፣ ቀስቃሽ፣ የሕግ ባለሙያና ፈላስፋ እንዲሁም የሃገሩ ቆንሲል የነበረውን ሲሴሮን የጠቀሱት የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ መሥራቾችና መሪዎች የኢትዮጵያዊ ዜጋነት ስሜትን በማጠናከርና በመብቶች ጉዳዮች ላይ የሚሠራ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ “የኢትዮጵያዊነት ኢንስቲትዩት” እያቋቋመ ነው።

ኢንስቲትዩቱና ድርጅቱም ከሥነ-ዜጋ ትምህርትና ኢትዮጵያዊ ሥነ-ምግባር የታሪክን እውነተኛ ምንጮች እስከመፈተሽ፣ የሃሰት ትረካዎችን እስከማጋለጥና ማስተካከል፣ በኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባትና በሃገራዊ ፍቅርና ክብር መተሣሰርን እስከ ማፅናት የሚደርስ ሥራ እንደሚያከናውኑ መሥራቾቹና መሪዎቹ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል።

ኢንስቲትዩቱና ድርጅቱም የያዟቸውን ዕቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ የሚውል ጥሪት ለማግኘት ያሰቡበትን ድጋፍ ለማሰባሰብ ከነኀሴ 13/2011 ዓ.ም ጀምሮ የ “ጎ ፈንድ ሚ” ዘመቻ እንደሚያካሂዱ ገልፀዋል።

ሙሉውን ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢትዮጵያዊነት - የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:40:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG