በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት ቀን


ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ
ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ

ዛሬ የሲቪል መብቶች ተሟጋቹ የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት ቀን ነው። በዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ክብረ በዓል ነው።

አሜሪካ የግለሰብን የልደት በዓል የምታከብረው ለሁለት ሰዎች ብቻ ነው፤ እንድም የሃገሪቱን መሥራች አባት ጆርጅ ዋሺንግተንን፤ አንድም የኪንግን። የዋሺንግተን ክብር “የፕሬዚዳንቶች ቀን” ተብሎ ስለሌሎቹም ፕሬዚዳንቶች የሚታሰብ ሲሆን የኪንግ ግን “የማርቲን ሉተር ኪንግ ቀን” ወይም በሙሉ ስማቸው ምኅፃር “ኤም ኤል ኬ ዴይ” ተብሎ በቀን መቁጠሪያ ላይ በይፋ ሠፍሯል።

ለዩናይትድ ስቴትስ ጥቁሮች ቀን ጨለማ በነበረበት ጊዜ፤ ጥቁር እንደምሉዕ ሰው በማይታይባቸውና በማይቆጠርባቸው በእነዚያ ቀናት ማርቲን ሊተር ኪንግ ጁኒየር እና ጓዶቻቸው የመሩት ሰላማዊ፤ ግን ጠንካራ ፅናትን የጠየቀ፣ መራር መስዋዕትነትን ያስከፈለ ብርቱ ትግል ሃገሪቱን ከጫፍ ጫፍ ያነቃነቀ፤ የድፍን ዓለምን ትኩረትም ያገኘ ነበር።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት ቀን
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:13 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG