በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰበር ዜና - በኅዳሴ ጉዳይ የጋራ መግለጫ ወጣ


የግብፅ፣ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፤ ዋሺንግተን ዲሲ፤ ረቡዕ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም.
የግብፅ፣ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፤ ዋሺንግተን ዲሲ፤ ረቡዕ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም.

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፤

የግብፅ፣ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክ የጋራ መግለጫ

የግብፅ፣ የኢትዮጵያና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ እንዲሁም ልዑኮቻቸው ከዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትርና ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም. ተገናኝተዋል። በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ አሞላል እና ማንቀሳቀስ (ኦፕሬሽን) ላይ አጠቃላይ፣ የትብብር፣ የተቀናጀ፣ ዘላቂና ሁሉም ተጠቃሚ ለሚሆኑበት ስምምነት እንዲሁም ይህንን ፅኑ አቋማቸውን በ2008 ዓ.ም. የመርኆች መግለጫ መሠረት ተግባራዊ የሚያደርጉበትን ግልፅ ሂደት ለመፍጠር ቁርጠኛነታቸውን ሚኒስትሮቹ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በውኃ ሚኒስትሮቻቸው ደረጃ የሚካሄዱ አራት መንግሥታዊ የቴክኒክ ስብሰባዎችን ለማድረግ የደረሱበትን ስምምነት አስታውሰዋል። የዓለም ባንክና ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እንዲሰጡና በየስብሰባዎቹ ላይም በታዛቢነት እንዲገኙ ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል። ሚኒስትሮቹ በተጨማሪም ስምምነቱን እስከ ጥር 6/2012 ዓ.ም. ለማጠናቀቅ ለመሥራት፣ እንዲሁም ኅዳር 28/2012 ዓ.ም. እና ጥር 4/2012 ዓ.ም. ሂደቱን ለመገምገምና ለመደገፍ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በሚደረጉ ሁለት ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ተስማምተዋል። እስከ ጥር 6/2012 ዓ.ም. ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ የ2008 ዓ.ምቱ የመርኆች መግለጫ አንቀፅ 10 ተግባራዊ እንዲሆን ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ስምምነታቸውን ሲያጠናቅቁ ለግብፅ፣ ለኢትዮጵያና ለሱዳን ሕዝቦች የአባይን የጎላ የልማት ትርጉም፣ የወሰን ተሻጋሪ ትብብርን አስፈላጊነት እና ስምምነት ላይ ለመድረስ ያላቸውን የጋራ ፍላጎት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

________________________________________________

ማስታወሻ

1. በዚህ ትርጉም ውስጥ ቀኖች ወይም ዓመቶች የተጠቀሱት በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ነው።

2. የ2008 ዓ.ምቱ የመርኆች መግለጫ አንቀፅ 10 ትርጉም እንደሚከተለው ይነበባል፤

“10. አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት መርኅ፤

ሦስቱም ሀገሮች በመርኆች መግለጫው አተረጓጎም ወይም አተገባበር ወቅት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በመልካም መንፈስ መርኅ ላይ ተመሥርተው በውይይቶች ወይም በድርድሮች ለመፍታት ቁርጠኛ ናቸው። ወገኖቹ አለመግባባቶቹን በውይይት ወይም በድርድር ለመፍታት ሳይቻላቸው ቢቀር ግልግል ወይም አሸማጋይ ሊጠይቁ ወይም ለርዕሳነ ብሄሮቻቸው ወይም ለጠቅላይ ሚኒስትሮቻቸው ሊያሳውቁ ይችላሉ።”

3. ከላይ የተቀመጡት ትርጉሞች ሁሉ የቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት የአማርኛ ክፍል ግርድፍ ትርጉሞች ናቸው። ለትክክለኛ መረጃ ማስረጃነት ካልሆነ በቀር በህጋዊ ሰነድነት ሊቀርቡ አይችሉም።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኅዳሴ ጉዳይ የጋራ መግለጫ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትዊት ለማየት ከታች የተመለከተውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፤

https://twitter.com/realDonaldTrump/status/1192157303753125888?s=20

የግብፅ፣ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክን የጋራ መግለጫ ለማየት ከታች የተመለከተውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፤

https://home.treasury.gov/news/press-releases/sm827

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG