ዋሺንግተን፤ ዲሲ —
ፕሬዚዳንቱ የሃገራቸውን ሁኔታ “ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጠንካራ ነው” ሲሉ የዴሞክራቲክ ፓርቲውን ምላሽ የሰጡት የሚሺጋን ገዥ ግሬቸም ዊትመር ግን “ሃገሪቱ ጥሩ የሆነችው ለከበርቴዎች እንጂ ለባለመካከለኛ ገቢው አሜሪካዊ አይደለም” ብለዋል።
በፕሬዚዳንቱ ንግግርና ከዴሞክራቲክ ፓርቲው በተሰጠው ምላሽ ላይ ምሁራን ለአሜሪካ ድምፅ ትንታኔ ሰጥተዋል።
በሰሜን ካሮላይና ኤ ኤንድ ቲ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ እና በቴክሳስ ኮሊን ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ መምህር ፕሮፌሰር ሞሐመድ ጣሂሮ ናቸው።
ሙሉውን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ